131 ሺህ የፌስቡክ ቤተሰቦች! እናመሰግናለን!
131𝐊 𝗙𝗮𝗰𝗲𝗯𝗼𝗼𝗸 𝗙𝗼𝗹𝗹𝗼𝘄𝗲𝗿𝘀! 𝗧𝗵𝗮𝗻𝗸 𝗬𝗼𝘂!
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ ተከታዮች ቁጥር 131 ሺህ መድረሱን ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው። ይህ ስኬት የእናንተ የቅርብ ክትትል፣ ንቁ ተሳትፎ እና ገንቢ አስተያየት ውጤት ነው። ከእኛ ጋር ለሆናችሁ፣ መረጃዎቻችንን ለተከታተላችሁ እና ሀሳባችሁን ላካፈላችሁን በሙሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
በቀጣይም የትምህርትና ስልጠና ጥራት የማረጋገጥ ተግባራት ፣ የእውቅና አሰጣጥ፣ የከፍተኛ ትምህርት ፈቃድ አሰጣጥ እና እድሳት፣ የዓለም አቀፍ እና የማህበረሰብ ት/ቤቶች ፈቃድ እና የፈቃድ እድሳት ፣የከፍተኛና የቴ/ክ/ሙ ተቋማት ክትትልና ቁጥጥር ፣የጥራት ኦዲት እና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና የአቻ ግምትን አሰራሮችን የተመለከቱ ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ይዘን እንቀርባለን። ገጻችንን ሼር (Share) በማድረግ ለሌሎችም ተደራሽ እንዲሆን የበኩላችሁን እንድትወጡ እንጋብዛለን!
የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት www. neta.gov.et ይከታተሉ ።