Skip to content
Newsroom

ማሳሰቢያ ለሁሉም የከፍተኛ ትምህርት መውጫና መግቢያ ፈተና አስፈታኝ ተቋማት በያሉበት ጉዳዩ፡- የ2019 ዓ.ም አጋማሽ የመውጫና መግቢያ ፈተናዎች ተፈታኞች ምዝገባ ጊዜን ስለማሳወቅ

ETA Education & Training Authority November 12, 2026 1 min read
ማሳሰቢያ ለሁሉም የከፍተኛ ትምህርት መውጫና መግቢያ ፈተና አስፈታኝ ተቋማት በያሉበት ጉዳዩ፡- የ2019 ዓ.ም አጋማሽ የመውጫና መግቢያ ፈተናዎች ተፈታኞች ምዝገባ ጊዜን ስለማሳወቅ

#ማሳሰቢያ
#ለሁሉም_የከፍተኛ_ትምህርት_መውጫና_መግቢያ_ፈተና_አስፈታኝ_ተቋማት
#በያሉበት
#ጉዳዩ_የ2019_አጋማሽ_የመውጫና_መግቢያ_ፈተናዎች_ተፈታኞች_ምዝገባ_ጊዜን_ስለማሳወቅ
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2019 ዓ.ም የከፍተኛ ትምሀርት መውጫና መግቢያ ፈተናዎችን
በተያዘው ዓመታዊ እቅድ መሠረት ለማስፈጸም ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ይታወቃል።
በመሆኑም የአጋማሽ ዓመቱ የመውጫና የመግቢያ ፈተናዎች ተፈታኞች ምዝገባ በራስ አገዝ የምዝገባ ሥርዓት
(Self –Registration System) የሚከናወን ሲሆን፣ የምዝገባ ጊዜያቱ እንደሚከተለው ነው።
#የተፈታኞች_የምዝገባ_ጊዜ
የመንግሥት ተቋማት የመውጫ ፈተና ህዳር 4-10/2019 ዓ.ም
የግል ተቋማት ድጋሚ ተፈታኞች መውጫ ፈተና ህዳር 11--17/2019 ዓ.ም
የድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGTA) ህዳር 10-30/2019 ዓ.ም
ሁሉም ተቋማት ተፈታኞቻቸውን በተያዘው የጊዜ ሰሴዳ መሠረት ለማስመዝገብ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎቻቸውን
በወቅቱ እንዲያጠናቅቁ እናሳስባለን። ለምዝገባ የሚከፈለው ክፍያም በተሻሻለው የክፍያ ተመንና በሚኒስትሮች
ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 593/2018 መሠረት ይሆናል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ፣ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የምዝገባ አስፈጻሚዎች አሰልጣኞች (TOT) ሥልጠና ቀደም ሲል
የወሰዱ ሲሆን፣ ለግልና ለክልል ከፍተኛ ትምሀርት ተቋማት የምዝገባ አስፈጻሚዎች ሥልጠና በቀን 04/03/2019
ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በበይነ መረብ ይሰጣል። የስብሰባ ማገናኛውም (Meeting Link) በprivate and Regional Higher Institution WhatsApp Group የሚለቀቅ በመሆኑ የተቋማት ኃላፊዎች ተገቢዎቹንና
የምዝገባ አስፈጻሚዎች በሥልጠናው እንዲያሳትፉና ምዝገባውን በተያዘው ፕሮግራም መሠረት እንዲያስፈጽሙ
በጥብቅ እናሳሰባለን።
የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት www. neta.gov.et ይከታተሉ ።

News Announcement
Share