Skip to content
Newsroom

በከፍተኛ እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት የክትትልና ቁጥጥር መመሪያ 987/2016 መሠረት በባለሥልጣኑ ከተፈቀደው የተማሪ ቁጥር በላይ መዝግቦ ሲያስተምር ስለተገኘ ተቋም፡-

ETA Education & Training Authority September 30, 2026 1 min read
በከፍተኛ እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት የክትትልና ቁጥጥር መመሪያ 987/2016 መሠረት በባለሥልጣኑ ከተፈቀደው የተማሪ ቁጥር በላይ መዝግቦ ሲያስተምር ስለተገኘ ተቋም፡-

በከፍተኛ እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት የክትትልና ቁጥጥር መመሪያ 987/2016 መሠረት በባለሥልጣኑ ከተፈቀደው የተማሪ ቁጥር በላይ መዝግቦ ሲያስተምር ስለተገኘ ተቋም፡-

✔️ማንኛውም ተቋም በባለሥልጣኑ ከተፈቀደው የተማሪ ቁጥር በላይ መዝግቦ ማስተማር አይችልም፤
✔️ተቋማት ከተፈቀደላቸው የተማሪ ቁጥር በላይ ቅበላ ማድረግ ሲፈለጉ ለባለሥልጣኑ ጥያቄ በማቅረብ ፈቃድ ማግኘት ይኖርባቸዋል ፤
✔️ከላይ የተቀመጠውን ድንጋጌ በመተላለፍ አንድ ተቋም ከተፈቀደለት የተማሪ ቁጥር እስከ 20% ጭማሪ አድርጎ ሲገኝ በትምህርት መስኩ ለ1 ዓመት አዲስ ተማሪ እንዳይቀበል ቅጣት ይጣልበታል፤
✔️ከተፈቀደለት የተማሪ ቁጥር ከ 20% በላይ ጭማሪ ተቀብሎ የተገኘ ከሆኑ በትምህርት መስኩ ለተከታታይ ለ2 ዓመታት አዲስ ተማሪ እንዳይቀበል ቅጣት ይጣልበታል፤ እና
✔️ከላይ የተጠቀሰውን የተላለፈ ተቋም የትምህርት መስክ እንዲዘጋ ይደረጋል።
የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት www. neta.gov.et ይከታተሉ።

News Announcement
Share