Skip to content
Newsroom

በከፍተኛ እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት የክትትልና ቁጥጥር መመሪያ 987/2016 መሠረት የመግቢያ መስፈርት ያላሟሉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ሲያስተምር የተገኘ ተቋም

ETA Education & Training Authority September 22, 2026 1 min read
በከፍተኛ እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት የክትትልና ቁጥጥር መመሪያ 987/2016 መሠረት የመግቢያ መስፈርት ያላሟሉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ሲያስተምር የተገኘ ተቋም

በከፍተኛ እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት የክትትልና ቁጥጥር መመሪያ 987/2016 መሠረት የመግቢያ መስፈርት ያላሟሉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ሲያስተምር የተገኘ ተቋም

✔️ማንኛውም ተቋም ስልጣን ባለው አካል የወጣ የቅበላ መስፈርት ያላሟሉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር አይችልም፤
✔️ተቋሙ ከተቀመጠው የቅበላ መስፈርት ውጪ ምዝገባ ባካሄደባቸው የትምህርት መስኮች ለ 2 ተከታታይ ዓመታት አዲስ ተማሪ እንዳይቀበል ቅጣት ይጣልበታል ፤
✔️ከላይ የተጠቀሰውን የተላለፈ ተቋም የቅበላ መስፈርት ያላሟላ የትምህርት መስክ እንዲዘጋ ይደረጋል፤
✔️የቅበላ መስፈርት ያላሟሉ ተማሪዎችን ያሰናብታል፤ በ 1 ወር ውስጥ ለባለሥልጣኑ ሪፖርት ያደርጋል፤ እና
✔️በዚህ መልክ የተገኙ የትምህርት ማስረጃዎች በማንኛውም መልኩ ተቀባይነት አይኖራቸውም ::
የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት www. neta.gov.et ይከታተሉ።

News Announcement
Share