በከፍተኛ እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት የክትትልና ቁጥጥር መመሪያ 987/2016 መሠረት አሳሳች ማስታወቂያ የሚያሰራጭ ተቋምን በተመለከተ:-
✔️ ማንኛውም ተቋም በካምፓስ፣ በመርሀ ግብር ወይም በትምህርት መስክ ከባለሥልጣኑ የከፍተኛ ትምህርት አገልግሎት ለመስጠት ፈቃድ ሳያገኝ ማንኛውንም ማስታወቂያ መስራትና ማሰራጨት የተከለከለ ነው፤
✔️ ከላይ የተጠቀሰውን ተላልፎ የተገኘ ተቋም ማስታወቂያውን ባስነገረበት መንገድ ማስተካከያ አድርጎ በአንድ ወር ውስጥ ለህዝብ ይፋ በማድረግ ለባለሥልጣኑ ሪፖርት እንዲያደርግ ይደረጋል፤ የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያም ይሰጠዋል፤
✔️ ከላይ በተጠቀሰውን መሠረት ተግባራዊ ባያደርግ ተቋሙ የተሳሳተ ማስታወቂያ ባስነገረበት ካምፓስ፣መርሀ- ግብር ወይም የትምህርት መስክ ለ2 ዓመታት የከፍተኛ ትምህርት አገልግሎትእንዳይሰጥ ቅጣት ይጣልበታል፤ እና
✔️ ከላይ የተጠቀሰውን የተላለፈ ተቋም የተሳሳተ ማስታወቂያ ባስነገረበት ካምፓስ ወይም መርሀ-ግብር ወይም የትምህርት መስክ እንዲዘጋ ይደረጋል፡፡
የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት www. neta.gov.et ይከታተሉ።
Newsroom
በከፍተኛ እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት የክትትልና ቁጥጥር መመሪያ 987/2016 መሠረት አሳሳች ማስታወቂያ የሚያሰራጭ ተቋምን በተመለከተ:-
ETA
Education & Training Authority
September 28, 2026
1 min read