ከኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መስፈርቶችን በተመለከተ የተሰጠ ማሳሰቢያ
✔️በቅድመ-ምረቃ እና በድህረ-ምረቃ መርሃ-ግብር ተመዝጋቢዎች የሚከተሉትን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡-
✔️የትምህርት ሚኒስቴር ለትምህርት ዘመኑ ያሳውቀውን የከፍተኛ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪ መግቢያ መስፈርት የመቁረጫ ነጥብ አሟልተው መገኘት አለባቸው፤
✔️ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋም የተመረቁ ባለሙያዎች በከፍተኛ ትምህርት በቅድመ-ምረቃ ደረጃ ለመመዝገብ በሠለጠኑበት የሙያ መስክ በደረጃ 4 ወይንም በቀድሞ 10+3 ወይንም 12+2 ዲፕሎማ ያጠናቀቁ ሆነው በሙያው ደረጃ 4 የብቃት ማረጋገጫ ምዘና (COC level 4) ተፈትነው ያለፉበትን ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤
✔️ለ2ኛ ዲግሪ ተመዝጋቢዎች በባለሥልጣኑ ህጋዊነቱ የተረጋገጠ የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፤ እንዲሁም National Graduate Admission Test (NGAT) የማለፊያ ውጤት ያላቸው መሆን አለባቸው ፡፡
✔️ከውጭ ሀገር የተገኘ የትምህርት ማስረጃ ለመግቢያ መስፈርት የሚያገለግለው በባለሥልጣኑ የአቻ ግምት ሲሰራለት ብቻ ይሆናል፡፡
✔️ከተጠቀሱ መመሪያዎች ውጪ ገብተው ለሚማሩ ኃላፊነቱ የተመዝጋቢዎቹ እና የተቋማቱ ብቻ መሆኑን እናሳስባለን።
የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት www. neta.gov.et ይከታተሉ።
Newsroom
ከኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መስፈርቶችን በተመለከተ የተሰጠ ማሳሰቢያ
ETA
Education & Training Authority
September 18, 2026
1 min read