ባለሥልጣኑ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ በመገኘት የክረምት በጎ ተግባራት መረሀ ግብር አከናውነ
የኢፊዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር በቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ በመገኘት የክረምት በጎ ተግባራት መረሀ ግብር አከናውኗል።
የባለሥልጣኑ የእውቅና ስታንዳርዴዜሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ድንኳና ንጉሳ ቀነኢ በመንግስት በተቀመጠ አቅጣጫ መሠረት የክረምት በጎ አድራጎት ሥራዎችን ለማከናወን በክልሉ መገኘታቸውን ገልጸው በዚህም ባለሥልጣኑ ለትውልድ ግንባታ መሠረት ከመጣል አንጻር ያለው ሚና የጎላ በመሆኑ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመገንባት መወሰኑን ገልጸዋል፡፡
በመረሀ ግብሩ ላይ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ተመስገን ዲሳሳ እና ምክትል የቢሮ ኃላፊው አቶ በሺር አብዱረሂም ፤ የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ (አደረጃጀት) ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኡሱማን አህመድ እና ሌሎች የሚመለከታቸው የክልሉ አመራሮች እንዲሁም የባለሥልጣኑ የጽ/ቤት ኃላፊ የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና በባለሥልጣኑ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና እና አጠቃላይ ትምህርት ፈቃድ አሰጣጥ መሪ ስራ አስፈጻሚ ተገኝተዋል፡፡
ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ትመህርት ቤት ግንባታ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ጎን ለጎን ለ500 ተማሪዎች የደብተር፣የቦርሳ፣ የእርሳስ እና የእስኪሪፕቶ ድጋፍ ተደርጓል። በመረሀ ግብሩ ባለሥልጣኑ የአሶሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሥራ እንቅስቃሴ ጉብኝት እና የችግኝ ተከላ ተደርጓል፡፡
ባለሥልጣኑ ባለፈው ዓመት በትምህርት ሚኒስቴር አስተባባሪነት በጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በመገኘት የአንድ አቅመ ደካማ ቤት ግንባታ እና የችግኝ ተከላ መረሀ ግብር ማከናወኑ ይታወሳል፡፡
የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት www. neta.gov.et ይከታተሉ።
Newsroom
ባለሥልጣኑ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ በመገኘት የክረምት በጎ ተግባራት መረሀ ግብር አከናውነ
ETA
Education & Training Authority
September 16, 2026
1 min read