#ጳጉሜ_2018
“የኢትዮጵያ ማንሰራራት”
ጳጉሜን፦ የስኬት ማጠቃለያ፣ የአዲስ ተስፋ መነሻ!
እየተጠናቀቀ በሚገኘው የ2018 ዓ.ም. የኢትዮጵያ የማንሰራራት ጉዞን የሚያመላክቱ በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል። እነዚህን ስኬቶች በማጠቃለል፣ የተገኙ ውጤቶችን በመገንዘብ እና ለቀጣይ የልማት ጉዞ በተስፋና በቁርጠኝነት ለመስካት የዘንድሮው ጳጉሜ በ**“የኢትዮጵያ ማንሰራራት” የጋራ መሪ መልዕክት ይከበራል።
የጳጉሜ ቀናት ልዩ መልዕክት
ጳጉሜ 1 — የእመርታ ቀን
የተመዘገቡ የእድገትና የእመርታ ውጤቶችን የምናከብርበት።
ጳጉሜ 2 — የማንሰራራት ቀን
ኢትዮጵያ በልማትና በእድገት የምትራመድበትን የማንሰራራት ጉዞ የምናጎለብትበት።
ጳጉሜ 3 — የጽናት ቀን
በፈተናዎች ውስጥ በጽናት በመቆም፣ የሀገር ግንባታ ጉዟችንን በቁርጠኝነት የምናስቀጥልበት።
ጳጉሜ 4 — የኅብር ቀን
በአንድነት፣ በመተባበርና በመከባበር የጋራ ሀገራዊ አቅማችንን የምናጠናክርበት።
ጳጉሜ 5 — የነገ ቀን
የተሻለች፣ የበለጸገችና ለትውልድ የምትተላለፍ ኢትዮጵያን ለመገንባት የነገ ራዕያችንን የምናድስበት።
ጳጉሜ የሚያልፈውን ዓመት ብቻ የምንሰናበትበት ሳይሆን፣ የተሳካውን የምናጠናክርበት፣ ከተሳሳትነው የምንማርበት እና ለተሻለ ነገ በአዲስ ተስፋና በተጨማሪ ቁርጠኝነት የምንነሳበት ወሳኝ ወቅት ነው።
“የኢትዮጵያ ማንሰራራት”
ስኬታችንን እናክብር፤ ትብብራችንን እናጠናክር፤ ነገያችንን በጋራ እንገንባ!
#ጳጉሜ2018
#የኢትዮጵያ_ማንሰራራት
#የእመርታ_ቀን
#የማንሰራራት_ቀን
#የጽናት_ቀን
#የኅብር_ቀን
#የነገ_ቀን
#ኢትዮጵያ
የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
Newsroom
#ጳጉሜ_2018 “የኢትዮጵያ ማንሰራራት” ጳጉሜን፦ የስኬት ማጠቃለያ፣ የአዲስ ተስፋ መነሻ!
ETA
Education & Training Authority
September 05, 2026
1 min read