በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በአቤቱታ እና ቅሬታ አፈታ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
ነሀሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ለባለሥልጣኑ ሠራተኞች በአገልግሎት አሰጣጥ፣በአቤቱታ እና ቅሬታ አፈታ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
የስልጠናው ዓላማ ከሥራ ክፍል ኃላፊዎች ጀምሮ በየደረጃው የሚገኙ ባለሙያዎችና ሠራተኞች የደንበኛ አያያዝ ክህሎታቸውን አዳብረው የተቋሙን የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት እና የደንበኞች እርካታን በተግባር እንዲያሳድጉ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት በባለሥልጣኑ የተቋማዊ ለውጥ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ደስታ ተ/አረጋይ ደንበኛን በፈገግታ፣ በትህትና እና በፍጥነት መቀበል የአገልግሎቱን ጥራት ግማሽ መንገድ የሚያሳካ መሆኑን ገልጸው አገልግሎት በሚሰጠበት ጊዜ ንቁ አዳማጭ መሆን ፤የተገልጋዩን ስሜት መረዳት ፤ግልጽ መረጃ መስጠት ፤ አዎንታዊ የአካል እንቅስቃሴ መገለጫ የሆኑትን ፈገግታና ትህትና ማሳየት፣ የሥራ ቦታን ለአገልግሎት ምቹና ዝግጁ ማድረግ ፣ ቀልጣፋ እና ፈጣን ምላሽ መስጠት እንዲሁም ደንበኛን በአግባቡ የማስተናገጃ ደረጃዎች የሆኑትን አቀባበል፣ ፍላጎት መለየት፣አገልግሎትን በስታንዳርዱ ላይ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ፤አቅጣጫ መጠቆም እና ደንበኛን በአክብሮትና በፍቅር መሸኘት የተገልጋዮችን እርካታ ለማሳደግ፣ ቅሬታዎችን ለመፍታት እና የአገልግሎት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በስልጠናው ላይ ስለደንበኛ አያያዝ መሠረቶች፤ ስለደንበኛን የማስተናገድ ደረጃዎች፤ ስለቅሬታዎችን የመደራደር ዘዴ፤ስለደንበኞች እርካታመለኪያ እና ስለአስቸጋሪ ግንኙነቶች ማስተዳደር ዙሪያ ሰፋ ያላ ማብራሪያና ገለጻ ተደርጓል፡፡
የቀረቡትን መነሻ ሀሳቦች መሠረት በማድረግ በተደረገው ውይይት ላይ ለተነሱ ሐሳብ አስተያየት እና ጥያቄዎች በባለሥልጣኑ የጽ/ቤት ኃላፊ በሆኑት በአቶ ታምሩ መስፍን፣ የሥራ አዘመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ በሆኑት ወ/ሮ ጥሩወርቅ ታደሰ እና የተቋማዊ ለውጥ ስራ አስፈጻሚ በሆኑት አቶ ደስታ ተ/አረጋይ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ተጠናቋል፡፡
የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት www. neta.gov.et ይከታተሉ።
Newsroom
በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በአቤቱታ እና ቅሬታ አፈታ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
ETA
Education & Training Authority
September 02, 2026
1 min read