በዓለም ዓቀፍ፣ የማህበረሰብ፣ ለትርፍ ያልተቋቋመና የበጎ አድራጎት ትምህርት ቤቶች ፈቃድ አሰጣጥ እና እድሳት መመሪያ 992/2016 መሠረት የማስፋፊያ ፈቃድ፡-
** ፈቃድ ተሰጥቶት በስራ ላይ ያለ የዓለም ዓቀፍ እና በውጭ ባለሃብት የተቋቋመ ትምህርት ቤት ደረጃውን ማሳደግ ሲፈልግ የኢንቨስትመንት ፈቃድን መሠረት አድርጎ ለባለሥልጣኑ ሲያመለክት የትምህርት ዓመቱ ከመጀመሩ ከ3 ወራት በፊት አስፈላጊው ምልከታ ተደርጎለት ጥያቄው አሳማኝ ሆኖ ሲገኝ የደረጃ ማሳደግ ፈቃድ ይሰጣል፤
*** ፈቃድ ተሰጥቶት በስራ ላይ ያለ የማህበረሰብ ትምህርት ቤት ደረጃውን ማሳደግ ሲፈልግ የትምህርት ዓመቱ ከመጀመሩ ከ3 ወራት በፊት ለባለሥልጣኑ በሚያቀርበው ጥያቄ መሠረት የትምህርት ቤቶች የሱፐርቪዥን ቡድን አስፈላጊው ምልከታ ተደርጎ ጥያቄው አሳማኝ ሆኖ ሲገኝ የማስፋፊያ ፍቃድ ይሰጣል።
የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት www. neta.gov.et ይከታተሉ።
Newsroom
በዓለም ዓቀፍ፣ የማህበረሰብ፣ ለትርፍ ያልተቋቋመና የበጎ አድራጎት ትምህርት ቤቶች ፈቃድ አሰጣጥ እና እድሳት መመሪያ 992/2016 መሠረት የማስፋፊያ ፈቃድ፡-
ETA
Education & Training Authority
August 31, 2026
1 min read