በትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና የአቻ ግመታ መመሪያ 990/2016 መሠረት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በውጭ ሀገር ተምረው የመጀመሪያ ዲግሪ በሀገር ውስጥ መማር ለሚፈልጉ ማቅረብ ያለባቸው ህጋዊ ሰነዶች፡-
የአቻ ግመታ አገልግሎትን ለማግኘት መሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ሆነው ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ህጋዊ ሰነዶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
** የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ የምስክር ወረቀት ወይም ዲፕሎማ፤
** ማስረጃው በተገኘበት ሀገር የዲግሪ የትምህርት መስክ ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያለው የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ የምስክር ወረቀት ወይም ዲፕሎማ እና ትራንስክሪፕት ፤
** የአመልካቹ የትምህርት ማስረጃ ትምህርቱን ከተከታተለበት ሀገር ስርዓተ ትምህርት ውጪ በሌላ ሀገር ስርዓተ ትምህርት መሠረት ከሆነ የመግቢያ ውጤቱ የሚወሰነው አመልካቹ ትምህርቱን በተከታተለበት የትምህርት ስርዓት ውጤት አወሳሰን መሠረት ይሆናል፤
** አመልካቹ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኝ እና የኢትዮጵያ መንግስት ፈቃድ በሰጠው ዓለም አቀፍ ወይም ማህበረሰብ ትምህርት ቤት የተማረ ከሆነ ከትምህርት ቤቱ የድጋፍ ደብዳቤ ያቀርባል፡፡
የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት www. neta.gov.et ይከታተሉ።
Newsroom
በትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና የአቻ ግመታ መመሪያ 990/2016 መሠረት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በውጭ ሀገር ተምረው የመጀመሪያ ዲግሪ በሀገር ውስጥ መማር ለሚፈልጉ ማቅረብ ያለባቸው ህጋዊ ሰነዶች፡-
ETA
Education & Training Authority
August 26, 2026
1 min read