Skip to content
Newsroom

የቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት የኘሮግራም ፈቃድ ዕድሳት ቅድመ ሁኔታዎች

ETA Education & Training Authority August 21, 2026 1 min read
የቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት የኘሮግራም ፈቃድ ዕድሳት ቅድመ ሁኔታዎች

የቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት የኘሮግራም ፈቃድ ዕድሳት ቅድመ ሁኔታዎች

** የፕሮግራሞቹ እድሣት /የፈቃድ እድሳት/ እንደ ፕሮግራም ቆይታው በተቋሙ ላይ በየጊዜው የሚደረግ ምርመራን መሠረት በማድረግ በየሶስት ዓመቱ የሚደረግ ሲሆን ይህንን ሳያመለክት የቀረ ማንኛውም ተቋም ፕሮግራሙ የማይታደስለት ይሆናል።
** ለተቋማት የኦዲት፣ እውቅና፣ ድጋፍና ኢንስፔክሽን ሊደረግ የሚችል ሲሆን በዚህም የተገኘው ሪፖርት መጨረሻ ላይ ለፈቃድ እድሣት በግብዓትነት የሚያገለግል ይሆናል።
** ከስልጠና ፕሮግራሙ ተመራቂዎች ውስጥ በፌደራል የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ብቁ ሆነው የተገኙትንና በግልም ሆነ በቅጥር ስራ ያገኙት ሰልጣኞች ብዛት ባለፉት ሦስት ዓመታት እየጨመረ የመጣ መሆኑን ማረጋገጥ።
** በፈቃድ ተመዝግበው ስልጠናቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ሰልጣኞች ምዘና አፈጻጸም ከ50% በታች ያስመዘገበ ተቋም የፈቃድ እድሳት አይሰጠውም።
** የተቋሙ ራእይ፣ ተልእኮ፣ ዓላማና አሰራር ከትምህርትና ስልጠና ፖሊሲው ጋር የተጣጣመ መሆን አለበት።
** የሙያ ደረጃዎችንና ስርዓተ ትምህርትን፣የአሰልጣኞችን ብቃት፣ የማሰልጠኛ እቃዎችን ፣ የስልጠና መሳሪያዎችን ፣ ቁሳቁሶችንና የመረጃ መሳሪያዎችን አስመልክቶ የተቀመጡትን ዝቅተኛ መለኪያዎች ማሟላት ይኖርበታል።
** ለስልጠና ሂደቱ ይረዳ ዘንድ እንደየሙያ ዓይነቱ ባህሪ ተቋሙ በምቹ ቦታ እና የተሟላ ማስተማሪያ ክፍሎች/ሰርቶ ማሳያ ቦታ/ /Laboratory/ /work shop/ ያሉት ስለመሆኑና በአስፈላጊው የማሰልጠኛ መሳሪያዎች ስለመደራጀቱ ዝግጅቱ ሁሉ ይህን የሚያሳይ መሆን አለበት።
** የሙያ ምዘናን የማሣለፍ መጠን ስልጠና ካጠናቀቁት ውስጥ ቢያንስ 50 በመቶ የሚሆኑት የሙያ ምዘናን ማለፍ ይኖርባቸዋል።
** እየጨመረ የመጣ ወደ ስራ የተሰማሩ ምሩቃን መጠን፤
**
የተሻሻለ የሙያ ደረጃን ካለ ተከትሎ የተሻሻለ ስርአተ ትምህርትና የማስተማሪያ የማሠልጠኛና የመማሪያ ማቴሪያሎች፤
** እየጨመረ የመጣ ብቃታቸው የተረጋገጠ መምህራን በደረጃና በመቶኛ፤
** ስልጠና አጠናቀው የወጡ ባለሙያዎች ያሉበትን ሁኔታ የሚያሣይ የጥናት ሪፖርት (Tracer Study) ፤
**
ፈቃድ ባለው የሒሣብ ባለሙያ የተደረገ የኦዲት ሪፖርት፤
** የተከማቸና የተሸጋገረ ቴክኖሎጂ፤
** በአካባቢው ካለ ኢንዱስትሪ ጋር የተደረገ ከኘሮግራሙ ጋር ተዛማጅነት ያለው የመግባቢያ ስምምነት አተገባበር፤
** በተቋሙ ድጋፍ አማካኝነት የተደራጁ የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ብዛት፤
** የጥራት አመራር ስርአት /Quality Management System/ ትግበራ የሚያሳይ መረጃ፤
** በዚህ የማረጋገጥ ሂደትም የአካባቢው የሰው ሀይል ገበያ መረጃ፣ የክትትል ሪፖርቶች፣ ጥራት ያለው የአመራር ስርአት ሪፖርትን አስመልክቶ የተሰጡ ግብረ መልሶች፣ አመላካች ጥናት ነው፡፡በተጨማሪም በዚህ የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ለአካል ጉዳተኛ ሰልጣኞች ተገቢውን እድል የሰጠ ተቋም ከመደበኛው መስፈርት ተጨማሪ ነጥብ ያገኛል፡፡
** በስልጠናው የተሳተፉ አካል ጉዳተኞች ብዛትና ከስልጠና በኋላ ስላሉበት ሁኔታ የሚገልፅ የጥናት ሪፖርት (Tracer Study)
የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።

News Announcement
Share