ባለሥልጣኑ በአረንጓዴ አሻራ እና በክረምት በጎ ተግባራት ድጋፍ ላይ ከግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ተወያየ
ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ ባለሥልጣኑ ከግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በአረንጓዴ አሻራ እና በክረምት በጎ ተግባራት ድጋፍ ላይ ውይይት አካሄደ ።
የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አህመድ አብተው ሊሰሩ የታቀዱት የአፀደ ህጻናት እና የአቅመ ደካማ ቤቶች ግንባታበቤንሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን መሆኑ ገልጸው በዚህ በጎ ተግባር የሚሳተፉ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የእውቅና ሰርተፍኬት ፤የሚሰጡት ድጋፍ ከታክስ ነጻ እንዲሆን የሚያደርግ የድጋፍ ደብዳቤ ፤ከተቋማቸው ተልእኮ አንጻር የማህበረሰብ አገልግሎት እና የጥናትና ምርምር ሥራዎች ጋር በተያያዘ የላቀ አበርክቶ እንዳለው አብራርተዋል።
የባለሥልጣኑ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታምሩ መስፍን በበኩላቸው ለሚገነቡት የአጸደ ህጻናት እና ለአቅመ ደካሞች የቤት ግንባታ በአጠቃላይ በትንሹ 24 ሚሊየን ብር እንደሚያስፈልግ ወጪው የህጻናቱን የደብተር፣ የእስክሪፐቶ እና ሌሎች የትምህርት ቁሳቁሶችን የሚሻፍን መሆኑን ገልጸዋል ።
የአድማስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት እና የኢትዮጵያ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ሞላ ጸጋዬ ተቋማት ፈቃድ እንዲያገኙ ማሟላት ከሚገባቸው መስፈርት አንዱ የማህበረስብ አገልግሎት በመሆኑ ተቋማቱ በተለያየ መንገድ የሚያደርጉትን የማህበሰብ አገልግሎት እንዲህ በተደራጀ መልኩ እንዲሆን ባለሥልጣኑ ከመንግስት የተረከበውን የአረንጓዴ አሻራ እና የክረምት በጎ ተግባራት ሀገራዊ ንቅናቄ ኃላፊት እንዲወጣ ለማስቻል በቦርዱ እና በተቋማቸው ስም ያላቸውን ዝግጁነት አረጋግጠዋል።
ተሳታፊዎች በበኩላቸው ለአረንጓዴ አሻራ እና ለክረምት በጎ ተግባራት የያዙት በጀት ባይኖርም ለትምህርት የሚደረግ ድጋፍ የዜግነት ግዴታ በመሆኑ በራሳቸውና በቀድሞ ተማሪዎች እንዲሁም በሌሎችም ድጋፍ የሚጠበቅባቸው ኃላፊት ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት www. neta.gov.et ይከታተሉ፡፡