Skip to content
Newsroom

‘የኢትዮጵያ የትምህርትና ስልጠና ብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ ከህግ ድንጋጌ ወደ ተግባራዊ አፈጻጸም መሸጋገር’ በሚል ርዕስ ሴሚናር ተካሄደ

ETA Education & Training Authority November 06, 2026 1 min read
‘የኢትዮጵያ የትምህርትና ስልጠና ብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ ከህግ ድንጋጌ ወደ ተግባራዊ አፈጻጸም መሸጋገር’ በሚል ርዕስ ሴሚናር ተካሄደ

‘የኢትዮጵያ የትምህርትና ስልጠና ብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ ከህግ ድንጋጌ ወደ ተግባራዊ አፈጻጸም መሸጋገር’ በሚል ርዕስ ሴሚናር ተካሄደ

‘የኢትዮጵያ ብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ ከህግ ድንጋጌ ወደ ተግባራዊ አፈጻጸም መሸጋገር’ በሚል ርዕስ ጥቅምት 27ቀን 2019 ዓ.ም በባለሥልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው ሴሚናር ላይ የመወያያ ሀሳብ ያቀረቡት በባለሥልጣኑ የብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ ዴስክ ኃላፊ የሆኑት አቶ ተስፋዝጊ መኮንን ብቃቶችን በትምህርት ውጤቶች አማካኝነት የመመደብ ስርዓት ዓላማ በዘርፎች መካከል ወጥ እና ግልጽ የብቃት ሥርዓት እንዲኖር በማድረግ ግልጽ፣ ተወዳዳሪ፣ ለጥራት መረጋገጥና መጎልበት የሚጠቅም ማድረግ በመሆኑ በርካታ ሀገራት ለትምህርት መሻሻል ሲሉ ብሔራዊ የብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፎችን እንደሚተገብሩ ዓለም አቀፍ ሁኔታ የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።
አቶ ተስፋዝጊ ባቀረቡት የውይይት መነሻ ሀሳብ ላይ ከተዳሰሱት ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል የኢትዮጵያ የብቃት ማዕቀፍ ማለት ምን እንደሆነ፤ ማዕቀፉ የያዛቸው እንኳር ጉዳዮች፤የማዕቀፍ አወቃቀርና ደረጃዎች፤ለባለድርሻ አካላት የሚያስገኛቸው ጥቅሞች፤ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ከማዕቀፉ አንጻር ያለው ወሳኝ ሚና፤ተግዳሮቶችና መልካም አጋጣሚዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ውይይቱን የመሩት በባለሥልጣኑ የእውቅና አሰጣጥ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ አበባየሁ ተረፈ እና የከፍተኛ ትምህርት ጥራት ኦዲት ከፍተኛ ባለሙያ ዶ/ር ውብነሽ ሽፈራው የሆኑት ብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ የትምህርት ደረጃ ምን ዓይነት የእውቀት፣የክህሎት እና የአመለካከት ደረጃ ሊኖር ይችላል የሚለውን ሐሳብ በተግባር ለማረጋገጥ የሚያስችልና ለሀገራችንም በጣም አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው የሀገራችን የብቃት ማእቀፍ የዓለም አቀፍ ተሞክሮን መሠረት ያደረገ በመሆኑ በየደረጃው የሚገኙ ሁሉም የባለሥልጣኑ ሠራተኞች የሚጠበቅባቸውን ድርሻ ሊወጡ እንደሚገባ ገልጸዋል ፡፡
ከተሳታፊዎች በርካታ ሀሳቦች እና አስተያየቶች ተነስተው ውይይት ተድርጎባቸዋል።
የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት www. neta.gov.et ይከታተሉ ።

Gallery

News Announcement
Share