በከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ፈቃድ እና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ መመሪያ 988/2016 መሠረትፈቃድ ወይም ፈቃድ እድሳት መሰረዝ፡-
** ፈቃድ አግኝቶ ሲሰራ የቆየ ማንኛውም ተቋም የፈቃድ እድሳት በወቅቱ ካልጠየቀ ባለሥልጣኑ ፈቃዱን ሊሰርዝ ይችላል፤
** ማንኛውም ተቋም ወይም ፕሮግራም በባለሥልጣኑ የተቀመጡ መስፈርቶችን አጓድሎ ሲገኝ እና በግምገማ ሲረጋገጥ የተሰጠው ፈቃድ ወይም ፈቃድ እድሳት ይሰረዛል፤
** ማንኛዉም በድንበር ተሻጋሪ ትምህርት መርሃ-ግብር የሚያስተምር የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በዉጭ ሀገር ያለዉ ተቋም እዉቅናዉ ካልታደሰ በሀገር ዉስጥ ያለዉ ተቋም የመርሃ ግብሩ እና የትምህርት መስኩ ፈቃዱ ይሰረዛል፤
** ማንኛውም ተቋም ወይም ፕሮግራም የትምህርት ጥራትን ካጓደለ፡ የከፍተኛ ትምህርት አሰጣጥ ህጎችን ከጣሰ እና የእግድ ቅጣት ተላልፎበት ካላሻሻለ ባለሥልጣኑ የሰጠውን ፈቃዱ ይሰረዛል፡፡
የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት www. neta.gov.et ይከታተሉ።
Newsroom
በከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ፈቃድ እና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ መመሪያ 988/2016 መሠረትፈቃድ ወይም ፈቃድ እድሳት መሰረዝ፡-
ETA
Education & Training Authority
September 14, 2026
1 min read