በትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና የአቻ ግመታ መመሪያ 990/2016 ረቂቅ ማሻሻያ ላይ የፊት ለፊት ወይም የገጽ ለገጽ የውይይት መድረክ ተካሄደ
ነሀሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ በትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና የአቻ ግመታ መመሪያ 990/2016 አንቀጽ 5 ንኡስ አንቀጽ 5 ላይ ረቂቅ ማሻሻያ ላይ ከትምህርት ማህበረሰብና ከባለድርሻ አካላት የፊት ለፊት ወይም የገጽ ለገጽ የውይይት መድረክ ተካሄደ።
የውይይት መድረኩን የመሩት የባለሥልጣኑ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታምሩ መስፍን ባለሥልጣኑ የማሻሻያውን ረቂቅ ማስታወቂያ ፤ የአስተያየት መስጫ ማስፈንጠሪያ ወይም ሊንክ በማዘጋጀት እና በተቋሙ የኢ-ሚይል አድራሻ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ከሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም አስተያየተቸውን እንዲሰጡ ለማድረግ ሰፊጥረት መደረጉን ገልጸው ባለሥልጣኑ የተጣለበትን የትምህርትና ስልጠና ጥራት የማረጋገጥ ታላቅ ሀገራዊ ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስችሉ የአሰራር ስርዓቶች የመቅረጽ እና አላሰራ ያሉ መመሪያዊች እንዲሻሻሉ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን አብራርተዋል።
የአድማስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት እና የኢትዮጵያ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ሞላ ጸጋዬ በበኩላቸው ባለሥልጣኑ የትምህርትን ጥራት ለማረጋገጥ እየሰራ ያለውን ሥራ የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል።
በመድረኩ የባለሥልጣኑ የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና አቻ ግመ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ሀብታሙ ገ/መድህን በረቂቅ ሰነዱ ላይ ያተኮረ ለውይይት መነሻ የሚሆን ሀሳብ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡
ከተሳታፊዎች የተለያዩ ሐሳቦች፣ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች ተነስተው ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት www. neta.gov.et ይከታተሉ፡፡