Skip to content
Newsroom

የትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ 800 ሚሊየን ችግኝ በአንድ ጀምብር የመትከል መረሀ ግብር አካሄዱ

ETA Education & Training Authority August 03, 2026 1 min read
የትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ 800 ሚሊየን ችግኝ በአንድ ጀምብር የመትከል መረሀ ግብር አካሄዱ
የትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ 800 ሚሊየን ችግኝ በአንድ ጀምብር የመትከል መረሀ ግብር አካሄዱ

የትምህርት ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት አመራርና ሠራተኞች በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ከተማ በምትገኘው ቢሾፍቱ ከተማ አካባቢ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አካሄዱ።
በጋራ ተስፋን እንትከል በሚል መሪ ሐሳብ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው 800 ሚሊየን ችግኝ በአንድ ጀምብር መረሀ ግብር ላይ የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ ባስተላለፉት መልዕክት የአረንጓዴ አሻራ ተነሳሽነት ለሀገራችን ሁለንተናዊ ልማትና ለዘላቂ የአካባቢ ጥበቃ ወሳኝ መሆኑን ፤ችግኝ መትከል ከራስ አልፎ ለቀጣይ ትውልድ የመልካም አካባቢ ውርስ ማስቀመጥ እና ከራስ አልፎ ለትውልድና ለሀገር ማሰብ የሰው ልጅ ትልቅነትን የሚያሳይ መለኪያ መሆኑን ገልጸው በዛሬው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የተተከሉት ችግኞች ከምግብ ምንጭነታቸው ባሻገር ለደን ልማት፣ ለአፈር ለምነት ጥበቃ እና ለአካባቢ ሥነ-ምህዳር መሻሻል ጉልህ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ በመሆናቸውየዘርፉ አመራሮችና ሠራተኞች እነዚህን ችግኞች በመትከል አርአያነታቸውን በተግባር ማሳየታቸው የሚደነቅ እና ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባ ነው ብለዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ ላይ የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ፤ የትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሕይወት ፤በኢፊዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የተቋማት ቁጥጥር ኢንስፔክሽን እና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሺሻይ አማረ እና የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ በቦታው በመገኘት ችግኝ በመትከል አሻራቸውን አኑረዋል።
የኢፊዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት www. neta.gov.et ይከታተሉ::
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር
በጋራ ተስፋን እንትከል!…
See more

Gallery

News Announcement
Share