Skip to content
Newsroom

የባለሥልጣኑ አመራሮች እና ሠራተኞች የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸምን ገመገሙ

ETA Education & Training Authority July 29, 2026 1 min read
የባለሥልጣኑ አመራሮች እና ሠራተኞች  የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸምን  ገመገሙ
የባለሥልጣኑ አመራሮች እና ሠራተኞች የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸምን ገመገሙ
------------------------------------------------------------------------------------------
ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም በባለሥልጣኑ ሊሰሩ የታቀዱ ዋና ዋና ግቦችን መነሻ በማድረግ በየሥራ ክፍሎቹ የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እና ግምገማ ተደርጓል።
በግምገማ መድረኩ የተቋማት ፈቃድ አሰጣጥና የጥራት ኦዲት፤የእውቅና እና ስታንዳርዳይዜሽን ፤የተቋማት ቁጥጥር፣ኢንስፔክሽን እና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ ፤የሥራ አመራር እና የአስተዳደር ዘርፎች በ12 ወራት ሊሰሯቸው የታቀዱ ዋና ዋና ግቦችን መነሻ በማድረግ በየሥራ ክፍሎቹ የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም ሪፖርት በባለሥልጣኑ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ በሆኑት በወ/ሮ አመለወርቅ ቀርቦ ሰፊ ውይይት እና እና ግምገማ ተደርጓል።
ባለሥልጣኑ በበጀት ዓመቱ በርካታ ውጤታማ ተግባራትን እንዳከናወነ የተገመገመ ሲሆን በተለይም በፈቃድ አሰጣጥና የጥራት ኦዲት ዘርፍ በአዲስ አበባ የሚገኙ ሁሉም የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዳግም ምዝገባ ስርዓት ውስጥ እንዲያልፉ መደረጉ እና የዳግም ምዝገባ ውሳኔ የያዘ ሪፖርት ለተቋማቱ እንዲደርስ መደረጉ ፤ በክልል የሚገኙ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዳግም ምዝገባ ስርዓት ውስጥ እንዲገቡ መደረጉ ፤ ለክልል መንግስታት ተጠሪ የሆኑ ተቋማት በዳግም ምዝገባ ስርዓት ውስጥ እንዲገቡ መደረጉ ፤ በፌደራል ደረጃ የሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በዳግም ምዝገባ ስርዓት ውስጥ እንዲገቡ መደረጉ እና በዳግም ምዝገባ ውሳኔ ቅሬታ ላቀረቡ ተቋማት ምላሽ መሰጠቱ፤ የጥራት ኦዲት ሥራን አስመልክቶ የከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና አካዳሚክ የጥራት ኦዲት የአሠራር ስርዓቶች ተዘጋጅተው እንዲጸድቁ መደረጉ፤ በአካዳሚክ የጥራት ኦዲት የአሠራር ስርዓቶች እና ስታንዳርዶች ዙሪያ ለአካዳሚክ የጥራት ኦዲተሮች ስልጠና መሰጠቱ፤ በራሳቸው ተነሳሽነት ለጠየቁ ተቋማት በተቋማዊና በፕሮግራም አካዳሚክ የጥራት ኦዲት አጠባበቅና የግል ግምገማ አዘገጃጀት ላይ ስልጠና መሰጠቱ፤የእርካታ ዳሰሳ ጥናት መካሄዱ፤በፕሮግራም የጥራት ኦዲት ስታንዳርድ መሠረት ተቋማት ግለ ግምገማ ማካሄዳቸው እና በአስር የከፍተኛ እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት የጥራት ኦዲት መከናወኑ ተገልጿል።
የአጠቃላይ ትምህርት ፈቃድ አሰጣጥ ላይ የተሠሩ ሥራዎች አፈጻጸም ያደገ መሆኑ በተለይም ለዓለም አቀፍ እና ለማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች አዲስ ፈቃድና የፈቃድ እድሳት ሥራ በእቅዱ መሠረት መከናወኑ ፤ በእውቅና እና ስታንዳርዳይዜሽን ዘርፍ ስለእውቅና አሰጣጥ ያለው ግንዛቤ መዳበሩ፣ የእውቅና አሰጣጥ ሥራ ዲጂታላይዝ መደረጉ ፣በርካታ ተቋማት የፕሮግራም እውቅና ይሰጠን የሚል ጥያቄ ማቅረባቸው እና ለሁለት ፕሮግራሞች ሙሉ እውቅና ለአምስት ዓመት ለአስራ አንድ ፕሮግራሞች ደግሞ በቅድመ ሁኔታ ለሶስት ዓመት እውቅና መሰጠቱ፤እንዲሁም በባለሥልጣኑ የስታንዳርዳይዜሽን ስራ ክፍል የአሰራር ስርዓቶች ከተቋሙ ዓላማና ግብ ስኬት አንጻር ተግባራዊነታቸው ላይ ክትትል መደረጉ፤ከ2014 ዓ.ም እስከ 2017 ዓ.ም የተዘጋጁ ማኑዋሎች፣ ጋይድላይኖች፤ስታንዳርዶች ፣ መመሪያዎች ደንቦች ተሰብስበው እንዲገመገሙ መደረጉ፤ የአሰራር ስርዓቶች እንዲዘጋጁ መደረጉ፤የትምህርትና ሥልጠና ጥራትን ለማረጋገጥና ለማጎልበት የሚያግዙ ዘጠኝ የትኩረት መስኮችና የጥናትና ምርምር እና ሀምሳ አንድ ቁልፍ የምርምር ትኩረቶች ተለይተዉ በባለሥልጣኑ የሥራ አመራር ጉባኤ እንዲጸድቅ መደረጉ እና የጆርናል ኤዲቶሪያል ፖሊሲ እና የጥናትናምርምር መምሪያ ልምድ ያላቸውን ባለሙያዎችን ከዩኒቨርሲቲዎችና ከምርምር ተቋማት በመጋበዝና በማሳተፍ ተዘጋጅተው ለማፅደቅ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተገልጿል።
በተቋማት ቁጥጥር፣ኢንስፔክሽን እና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ ዘርፍ የተቋማት የክትትልና ቁጥጥር ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉ እና የኢንስፔክሽን ሥራ አፈጻጸም ጥሩ ደረጃ ላይ ያለ መሆኑ እንዲሁም የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና የአቻ ግመታ አገልግሎት አሰጣጥን መሻሻል በመቻሉ ከበርካታ የመንግስት እና የግል ተቋማት የሠራተኞቻችን የትምህርት ማስረጃ የይረጋገጥልን ጥያቄ መቅረቡ እና በህብረተሰቡ ዘንድ ያለው በግል የራስን ትምህርት ማስረጃ የማረጋገጥ ፍላጎትና ተነሳሽነት በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩ እንዲሁም ባለሥልጣኑ ከመሶብ የአንድ ማእከል አገልግሎት ጋር በመቀናጀት ለበርካታ የትምህርት ማስረጃዎች ማረጋገጫ የሰጠና እና የአቻ ግመታ ሥራ ያከናወነ መሆኑ፤ በሥራ አመራር እና በአስተዳደር ዘርፉም የተቋሙ ዋና ዋና የሥራ ዘርፎች በመደገፍ ውጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻል የተሠሩ ሥራዎች ጥሩ አፈጻጸም ላይ መሆናቸው ተገልጿል።
የባለሥልጣኑን ተቀባይነት ከፍ ለማድረግ የሚያስችለው የውስጥ ጥራት ኦዲት ስራ ከኢትዮጵያ ስታንዳር ኢንስቲትዩት ጋር በጥራት አስተዳደር ሥርዓት ላይ የተመሠረተ የቴክኒክ ድጋፍ ለማግኘት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈርሞ ወደ ሥራ መገባቱ እና ለማኔጅመንትና ለተቋቋመው ግብረ ሀይል የዓለም አቀፍ የጥራት አመራር ስርዓት ISO9001:2015 ለመተግበር የሚያስችል ስልጠና መሰጠቱ፣የሥራ ክፍሎችን የአሰራር ስርዓትን ለማሳለጥ የሚያግዙ ማንዋሎች፣የተለያዩፎርማቶች፣ፕሮሲጀሮች፣ቼክሊስቶች፣ኳሊቲኦብጀክቲቭ፣ሪስክ አይደንትፊከሽና አሰስመንት፣ፖሊሲ እና ሌሎችም ተዘጋጅተው በየሥራ ክፍሎች የተገመገሙ መሆኑ በውይይቱ እና በግምገማ መድረኩ ተብራርቷል:።
የግምገማ መድረኩን የመሩት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አህመድ አብተው በበኩላቸው መድረኩ ያለፉት ሥራዎች የተገመገሙበት ፤የቀሩ ሥራዎች የሚከናወኑበት እና ለቀጣይ በጀት ዓመት የሚሆን እቅድ የሚዘጋጅበት መሆኑን ገልጸው ባለፈው በጀት ዓመት ሁሉም የሥራ ክፍሎች ያቀደቱን ሥራ ሙሉ በሙሉ ያከናወኑበት፤ለተቋሙ ወሳኝ የሆኑ የሥራ ክፍሎችን የማጠናከር ሥራ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት የተከናወነበት፤ቀደም ሲል ፈቃድ
የተሰጣቸው ተቋማት ወደ ጥሩ ቁመና እንዲመጡ እና አዳዲስ ተቋማት ጤናማ ሆነው እንዲወለዱ ሰፊ ሥራ የተሠራበት መሆኑን ገልጸው በበጀት ዓመቱ የተበታተኑ ሥራዎች ወደ አንድ እንዲመጡና ተናባቢ እንዲሆኑ በተቋሙ ውስጥ በላቀ መግባባትና ቁርጠኝነት መሠራቱን ገልጸዋል ፡፡ የባለሥልጣኑን የውስጥ አሰራር ጥራት በማረጋገጥ ረገድ የዓለም አቀፍ የጥራት አመራር ስርዓት ISO9001:2015 ትግበራ መጀመሩ እና የበሰለ የጥራት ኦዲት ሪፖርት ዝግጅት መጀመሩ በበጀት ዓመቱ ከተከናወኑት ዐበይት ተግባራት መካከል የሚጠቀሱ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ ተቋማት በአመሰራረታቸው፣በቆይታቸው እና በደረሱበት ደረጃ ለመለየት የሚያስችል የኦዲት፣የእውቅና አሰጣጥ እና የኢንስፔክሽን ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት እና ባለሥልጣኑ ተዓማኒነትን፣ግልጸኝነትን እና ተጠያቂነትን መሠረት ያደረገ ለውጥ በማምጣት ለትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ መሠረት የሆነውን የለውጥ ስራ ማጠናከር በቀጣይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት የሚሰራ ገልጸዋል ፡፡
የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት www. neta.gov.et ይከታተሉ፡፡
News Announcement
Share