የከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ፈቃድ እና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ መመሪያ 988/2016 መሠረት የፕሮግራም መሰረታዊ ጉዳይ ማለት:-
#የፕሮግራም_መሰረታዊ_ጉዳይ
** ማንኛውም ተቋም አዲስ ፕሮግራም ለመክፈት ወይም ነባሩን ፕሮግራም ለማስቀጠል የፍላጎት ዳሰሳ፣ የገበያ ጥናት እና ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ አውደ ጥናት ማካሄድ ይኖርበታል፤
** ለግል የከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት የተቋምና የፕሮግራም ፈቃድ የሚሰጠው የወጡ መስፈርቶች አሟልተው ሲገኙ ብቻ ይሆናል፤
** የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚከፍቷቸው ፕሮግራሞች የወጡ የመመዘኛ መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፤
** ለማንኛውም ተቋም የሚሰጥ ፈቃድ የሚያገለግለው በባለሥልጣኑ ተገምግሞ ለተፈቀደለት ካምፓስ፣ የትምህርት መስክ እና ጊዜ ብቻ ይሆናል፤
** ባለሥልጣኑ ለማንኛውም ተቋም ፈቃድ ሲሰጥ በማንኛውም የትምህርት መስክና መርሃ ግብር የተማሪ ቁጥር ገደብ የሚኖረው ይሆናል፤
**ማንኛውም ተቋም የጤና እና የህክምና የትምህርት መስኮችን መስጠት የሚችለው በመደበኛ መርሃ ግብር ብቻ ይሆናል፤
** ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በርቀት ትምህርት መርሃ ግብር ማስተማር የሚችለው በመጀመሪያ ዲግሪ ብቻ ይሆናል፤
* * ማንኛውም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የመምህርነት እና የህግ ትምህርት ዘርፎችን ማስተማር አይችልም፤
** ማንኛውም የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋም የትኛውንም ስልጠና በርቀት መርሃ ግብር ማሰልጠን አይችልም፤
** ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በህክምና ዶክትሬት እና በስፔሻሊቲ ትምህርት ፈቃድ ለማግኘት ተቋሙ የማስተማሪያ ሆስፒታል ሊኖረው ይገባል፤
** ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ በተቋም ደረጃ የጸደቀ ስርዓተ ትምህርት የፈቃድ ጊዜው ሳያበቃ ከባለሥልጣኑ ፈቃድ ውጪ የስርዓተ ትምህርት እና የዲግሪ ስያሜ ለውጥ ማድረግ አይችልም፤
** በተቋም ወይም በካምፓስ ደረጃ በለሥልጣኑ ተገምግሞ የጸደቀ ስርዓተ ትምህርት የፈቃድ ወይም ፈቃድ እድሳት ጊዜው እስካላበቃ ድረስ በተመሳሳይ ተቋም በሌሎች ካምፓሶች መተግበር ወይም መጠቀም ይችላል፤
** የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሁሉም የትምህርት መርሃ-ግብሮች ፈቃድ ሲጠይቁ ስርዓተ-ትምህርቱ በባለሥልጣኑ ከመስክ ምልከታ በፊት ቀድሞ መገምገም እና ተገቢ ማስተካከያ ተደርጎ መፅደቅ ይኖርበታል፤
** ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በልዩ ሁኔታ ኮርሱን ለመስጠት ሌላ አማራጭ የለም ተብሎ ሲታሰብ ባለስልጣኑ ትምህርቱ በብሎክ ኮርስ እንዲሰጥ ሊፈቅድ ወይም ሊወስን ይችላል፡፡
የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት www. neta.gov.et ይከታተሉ።
Newsroom
የከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ፈቃድ እና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ መመሪያ 988/2016 መሠረት የፕሮግራም መሰረታዊ ጉዳይ ማለት:-
ETA
Education & Training Authority
July 23, 2026
1 min read