ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያ

ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያ =============== መስሪያቤታችን የኢፌዴሪ ትምህርት ስልጠና ባለስልጣን ከዚህ በላይ በተዘረዘሩት ክፍት የሥራ መደቦች ላይ ባለሙያዎችን አወዳድሮ በዝውውር መቅጠር ይፈልጋል። #ማሳሰቢያ፡- 1 . ከዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታ በላይ የትምህርትና የስራ ልምድ ማስረጃ ያላቸው አመልካቾች ማመልከት ይችላሉ፡፡ 2 .የምዝገባ ጊዜ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የስራ ቀናቶች ይሆናል፡፡ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ የዲግሪ የትምህርት ማስረጃ የሚያቀርቡ አመልካቾች የመውጫ ፈተና ያለፉበትን መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ 3. ከግል ተቋማት የሚቀርቡ የስራ ልምድ ማስረጃዎች የስራ ግብር የተከፈለባቸው መሆን ይኖርባቸዋል። 4. አመልካቾች ለሚያቀርቡት የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃ ህጋዊነት ኃላፊነት ይወስዳሉ። 5. ለፈተና ለሚመለመሉ አመልካቾች ፈተና የሚሰጥበት ቀንና ቦታ በማስታወቂያ የሚገለፅ ይሆናል። 6. የምዝገባ አድራሻ፡- አዲስ አበባ በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ሽሮ ሜዳ ከአሜሪካ ኢምባሲ ፊት ለፊት የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።