በከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተቋም እና የፕሮግራም እውቅና አሰጣጥ መመሪያ 991/2016 መሠረት የእውቅና አሰጣጥ ካውንስል ፤ ገምጋሚ ባለሙያ፤ ገምጋሚ ባለሙያ እና የጥቅም ግጭት ፡-
---------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
በዋና ዳይሬክተሩ የሚሰየም፣ የተቋም እና የፕሮግራም እውቅና ሪፖርት እና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ የሚያጸድቅ አካል ነው።
በተቋም እና በፕሮግራም እውቅና ግምገማ ላይ የሚሳተፍ የባለሥልጣኑ የእውቅና አሰጣጥ ባለሙያ ነው።
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚያስተምር፣ በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች
የሚሰራ፣ የሙያ ማህበራት አባላት የሆነ እና በባለሥልጣኑ ስልጠና ወስዶ ከእውቅና አሰጣጥ ባለሙያዎች ባለሙያዎች ጋር በመሆን አንድን ተቋም ወይም ፕሮግራም ለመገምግም የሚሳተፍ ነው።
በገምጋሚ ቡድኑ ወይም በውሳኔ ሰጪው አባል እና በተገምጋሚው ተቋም መካከል የተቋም ወይም የፕሮግራም እውቅና ግምገማን ገለልተኛ ሆኖ እንዳያከናውን ሊያደርግ የሚችል ሁኔታ ነው።
የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት www. neta.gov.et ይከታተሉ።