ከኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣልን ጋር በመተባበር ለፌዴራልና ለክልል ማረሚያ ቤት ለትምህርትና ስልጠና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ
ከኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣልን ጋር በመተባበር ለፌዴራልና ለክልል ማረሚያ ቤት ለትምህርትና ስልጠና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ ==== === ================================ ዝዋይ ግንቦት 29/2018ዓ.ም. (የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን) የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ከኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣልን ጋር በመተባበር ከፌዴራልና ከክልል ማረሚያ ቤት ለተውጣቱ የትምህርትና ስልጠና ባለሙያዎች ከግንቦት 27 -29/2018ዓ.ም. ድረስ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል። በስልጠናው የመክፈቻ ሥነ ስርዓት ላይ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ጀኔራል ሉባባ ጀማል እንደተናገሩት የህግ ታራሚዎችን አርሞና አንጾ አምራችና ህግ አክባሪ ዜጋ ሆነው እንዲወጡ ለትምህርትና ስልጠና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ በኮሚሽኑ የሚሰጡ ስልጠናዎች ከህግ ታራሚዎችን በተጨማሪ አባላትን ማካተት እንደለበት በተቋሙ ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ በግልጽ መቀመጡን የተናገሩት ም/ኮሚሽነሯ ለማረም ማነጽና ተሃድሶ ልማት ባለሙያዎች የሚሰጡ ስልጠናዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡ የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣልን የቴክኒክና ሙያ ፍቃድ አሰጣጥ ዴስክ ኃላፊ አቶ ብርሀነ መስቀል መላክ በበኩላቸው ስልጠናው ኮሚሽኑ የትምህርትና ስልጠና ፍቃድ ለማግኘት ምን ማሟላት እንደሚገባውና ምን አይነት ዶክመንት ማዘጋጀት እንዳለበት የሚያስችል መሆኑን አመላክተዋል። የትምህርት ተቋማት የፍቃድ ጥያቄ አቀራረብ ሂደቶችን፣ ፍቃድና እድሳት እንዴት እንደሚሰጥ፣ ፍቃድ ለመጠየቅ ዝቅተኛ መስፈርቶች ምን እንደሆኑ ሰልጣኞች ግንዛቤ ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡ ከስልጠና ተሳታፊዎች መካከል አቶ አበባው አበበ እና ዋ/ኢ/ር ደረጄ ብራቱ አሰራራቸውን እንዴት ማዘመን እንዳለባቸው ከእነሱ አስተምህሮ አንፃር ሰልጣኞችን በምን አግባብ ማስተማር እና መመዘን እንዳለባቸው ግንዛቤ ማግኘታቸውን ገልፀዋል፡፡ በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ የሐራ ደንበል የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅን በመጎብኘት የልምድ ልውውጥ መደረጉን ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።
