የፌዴራል መንግስት አስፈፃሚ አካላት ስልጣን እና ተግባር ለመወሰን የወጣ አዋጅ 1263/2014 ዓ.ም እና የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣንን ለማቋቋም በሚኒስትሮች ምክርቤት በወጣ ደንብ ቁጥር 515/2014 ዓ.ም መሰረት በተሰጠው ስልጣን እና ተግባር የትምህርት ጥራትና አግባብነት ለማስጠበቅ እና ለመከታተል ያስችለው ዘንድ በመመሪያ 987/2016 ዓ.ም አንቀፅ 17 ንኡስ አንቀፅ 2 መሰረት ተቋማት የተመራቂ ተማሪዎችን መረጃ ወቅቱን ጠብቃችሁ ለባለስልጣኑ መላክ እንዳለባችሁ ተደንግጓል፡፡
በመሆኑም በተቋማችሁ ፈቃድ በተሰጣችሁ የትምህርት መስኮች፣የትምህርት ደረጃ፣መርሃ ግብር እና ካምፓስ የተመረቁ ተማሪዎችን መረጃዎች በድህረ ምረቃ ደረጃ እና በመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች መውጫ ፈተና ያለፉ ብቻ ከዚህ በፊት በተላከው ቅጽ መሰረት ዝርዝር መረጃውን ከመጋቢት 16/2017 ዓ.ም እስከ መጋቢት 30/2017 ዓ.ም በሶፍት እና በሃርድ ኮፒ እንድትልኩ እናሳስባለን፡፡
በፊስቡክ - https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም - https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት Www.neta.gov.et ይከታተሉን፡፡
Newsroom
ማሳሰቢያ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት ጉዳዩ፦ የተመራቂ ተማሪዎችን ዝርዘር መረጃ እንድትልኩ ስለማሳሰብ ይሆናል፤
ETA
Education & Training Authority
March 27, 2025
1 min read