ማሳሰቢያ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት ጉዳዩ፡- የተማሪዎቻችሁን መረጃና ማስረጃ አቀራረብን ይመለከታል፤

የፌዴራል መንግስት አስፈፃሚ አካላት ስልጣን እና ተግባር ለመወሰን የወጣ አዋጅ 1263/2014 ዓ.ም እና የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ለማቋቋም በሚኒስትሮች ምክርቤት በወጣ ደንብ ቁጥር 515/2014 ዓ.ም መሰረት በተሰጠው ስልጣን እና ተግባር የትምህርት ጥራትና አግባብነት ለማስጠበቅ እና ለመከታተል ያስችለው ዘንድ በመመሪያ 987/2016ዓ.ም አንቀፅ 17 የተማሪ መረጃ አያያዝ፣ አጠባብቅና አላላክን በተመለከተ ተደንግጓል፡፡ በመሆኑም በእርሱ ለመግለፅ እንደተሞከረው የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈቃድ ባገኙት የትምህርት መስክ፣ ካምፓስ፣ የትምህርት ደረጃ፣ መርሃ ግብር እና ፈቃድ ጊዜ ገደብ ተምሮ የተመረቁ ዜጎችን ግዴታቸውን እስከተወጡ ድረስ መብታቸውን ጠብቆ ከማስተማር ባሻገር የሚፈልጉት አስፈላጊ መረጃ እና ማስረጃ በአስተማራቸው ተቋማት በኩል መላክ እንዳለበት ይታወቃል፡፡ ስለሆንም ከተቋማችሁ የተመራቁ ተማሪዎቻችሁ ከተቋማችሁም ሆነ ከባለስልጣኑ የሚፈልጉትን ማንኛውም አገልግሎት በተቋማችሁ በኩል የተወከለ አካል/ህጋዊ ውክልና ያለው የተማሪ/ዎችን ጉዳይ ተከታትሎ እንዲያስፈፅም/ላቸው እናሳስባለን፡፡ በፊስቡክ - https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም - https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www.neta.gov.et ይከታተሉን፡፡