በከፍተኛ እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት የክትትልና ቁጥጥር መመሪያ 987/2016 መሠረት በባለሥልጣኑ ከተፈቀደው የተማሪ ቁጥር በላይ መዝግቦ ሲያስተምር ስለተገኘ ተቋም፡-
---------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
** ማንኛውም ተቋም በባለሥልጣኑ ከተፈቀደው የተማሪ ቁጥር በላይ መዝግቦ ማስተማር አይችልም፤
** ተቋማት ከተፈቀደላቸው የተማሪ ቁጥር በላይ ቅበላ ማድረግ ሲፈለጉ ለባለሥልጣኑ ጥያቄ በማቅረብ ፈቃድ ማግኘት ይኖርባቸዋል ፤
** ከላይ የተቀመጠውን ድንጋጌ በመተላለፍ አንድ ተቋም ከተፈቀደለት የተማሪ ቁጥር እስከ 20% ጭማሪ አድርጎ ሲገኝ በትምህርት መስኩ ለ1 ዓመት አዲስ ተማሪ እንዳይቀበል ቅጣት ይጣልበታል፤
** ከተፈቀደለት የተማሪ ቁጥር ከ 20% በላይ ጭማሪ ተቀብሎ የተገኘ ከሆኑ በትምህርት መስኩ ለተከታታይ ለ2 ዓመታት አዲስ ተማሪ እንዳይቀበል ቅጣት ይጣልበታል፤ እና
** ከላይ የተጠቀሰውን የተላለፈ ተቋም የትምህርት መስክ እንዲዘጋ ይደረጋል።
የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።
Newsroom
በከፍተኛ እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት የክትትልና ቁጥጥር መመሪያ 987/2016 መሠረት በባለሥልጣኑ ከተፈቀደው የተማሪ ቁጥር በላይ መዝግቦ ሲያስተምር ስለተገኘ ተቋም፡-
ETA
Education & Training Authority
January 12, 2026
1 min read