ባለሥልጣኑ ከኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ጋር የሥራ ውል ስምምነት ተፈራረመ

ባለሥልጣኑ ከኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ጋር የሥራ ውል ስምምነት ተፈራረመ ------------------------------------------------------------------------ ታህሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በጥራት አስተዳደር ሥርዓት ላይ የተመሠረተ የቴክኒክ ድጋፍ ለማግኘት የሚያስችል ስምምነት ከኢትዮጲያ ደረጃዎች ኢኒስቲትዩት ጋር ተፈራረመ፡፡ የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የእውቅና እና ስታንዳርዳይዜሽ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ድንኳና ንጉሳ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንዳሉት ስምምነቱ የጥራት አመራር ሥርዓት ISO9001:2015 መሠረት በማድረግ ባለሥልጣኑ በትምህርት ጥራት ላይ እየሰራ ያለውን የአሰራር ስርዓት ፈትሾ ለማስተካከል እና ከፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጋር በመሆን እየተሰራ ያለውን የሪፎርም ሥራ ከፍ ወደ አለ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጲያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሠረት በቀለ በበኩላቸው የቴክኒክ ድጋፍ የሚፈልግ ተቋም መጀመሪያ የራሱን ኃላፊነት በመወጣት ረገድ ጠንካራ ቁርጠኝነት ማሳየት እንዳለበት ገልጸው እንደዚህ ዓይነቱ ስምምነት የተቋምን የሥራ አፈጻጸም ለማሻሻል፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ እና ከብሔራዊና ከዓለም አቀፍ ደረጃዎች ጋር የተጣጣመ እንዲሆን ለማድረግ ከፍተኛ ጥቅም እንደሚኖረው ግልጸዋል ። በኢትዮጲያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት የስልጠናና ቴክኒክ ድጋፍ መሪ ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ መንግስቱ ተፈራ የአመራርሮች ቁርጠኝነት እና ጊዜ መስጠት ISO9001:2015 በአንድ ተቋም ውስጥ ለመተግበር መሠረታዊ ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል ። የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ ።