ለመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የጥራት አጠባበቅ ዳይሬክተሮችና ለአካዳሚክ ፕሮግራም ኦፊሰረሮች በአካዳሚ ፕሮግራም ጥራት ኦዲት ሪቂቅ ስታንዳርድ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
ለመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የጥራት አጠባበቅ ዳይሬክተሮችና ለአካዳሚክ ፕሮግራም ኦፊሰረሮች በአካዳሚ ፕሮግራም ጥራት ኦዲት ሪቂቅ ስታንዳርድ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ ---------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------- ታህሳስ 24 ቀን 2018 ዓ.ም በባለሥልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ ከመቶ በላይ ለሚሆኑ የመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የጥራት አጠባበቅ ዳይሬክተሮችና ለአካዳሚክ ኘሮግራም ኦፊሰረሮች በአካዳሚ ፕሮግራም የጥራት ኦዲት ሪቂቅ ስታንዳርድ ላይ በበይነመረብ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡ በኢፊዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የጥራት ኦዲት መሪ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ወ/ሮ ትእግስት ኃ/ስላሴ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ዓላማ ለተዘጋጀው የአካዳሚ ፕሮግራም ጥራት ኦዲት ሪቂቅ ስታንዳርድ ማሻሻያ ግብአት ለመሰብሰብ መሆኑን ገልጸው የአካዳሚ ፕሮግራም ጥራት ኦዲት ሪቂቅ ስታንዳርድ 11 ስታንዳርዶችን፣ ጋይድላይኖች እና ውጤት አመላካቾች የያዘ መሆኑን አስረድተዋል ፡፡ ወ/ሮ ትእግስት የአካዳሚ ፕሮግራም ጥራት ኦዲት ሪቂቅ ስታንዳርድ ይዘትን በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን የስታንዳርዱ አስፈላጊነት ፣የስታንዳርድ ዝግጅት ሂደቶችና መርሆዎች ፤የፕሮግራም ጥራት ኦዲት ስታንዳርዶች ፤የፕሮግራም ጥራት ኦዲት አደረጃጀት ፤ የADRI ሞዴል እና ትግበራን በተመለከተ ሰፊ ማብራሪያ እና ገለጻ አድርገዋል ፡፡ የቀረቡትን መነሻ ሀሳቦች መሠረት በማድረግ በተደረገው ውይይት ላይ ለተነሱ ሐሳብ አስተያየት እና ጥያቄዎች በኢፊዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የጥራት ኦዲት መሪ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ወ/ሮ ትእግስት ኃ/ስላሴ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ተጠናቋል፡፡ የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።
