ለባለሥልጣኑ ሴት አመራሮች እና ከፍተኛ ባለሙያዎች አመራርን የማብቃት ስልጠና ተሰጠ
ከየካቲት 6 እስከ 10 ቀን 2017 ዓ.ም በአዳማ ከተማ የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ለባለሥልጣኑን ሴት አመራሮች እና ለከፍተኛ ባለሙያዎችሲሰጥ የነበረው አመራርን የማብቃት ስልጠና ተጠናቋል፡፡ የሥልጠና መረሀ ግብሩን ያስጀመሩት እና በማጠቃለያውም ላይ መልእክት በማስተላለፍ የተዘጋጀውን የምስክር ወረቀት ለስልጠናው ተሳታፊዎች የሰጡት የባለሥልጣኑ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዝናቡ ሀምሳሉ ባለሥልጣኑ የሴቶችን የአመራርነት ብቃት ለማሳደግ ታቅደው እየተከናወኑ ከሚገኙ ተግባራት መካከል ይህ ስልጠና አንደኛው እና ወሳኙ መሆኑን ገልጸው፤ ለዚህም ባለሥልጣኑ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በጀት መድቦ እና ለሥልጠናዊ አስፈላጊ የሆኑት ግብዓቶች አሟልቶ ሴት አመራሮቹ ያለባቸውን ጊዜ የማይሰጥ የሥራና ማህበራዊ ኃላፊት ወደ ጎን ትተው በአመራርነት ረገድ አቅማቸውን ለማሳደግ እና ለመግንባት ቅድሚያ በመስጠት ከባለሥልጣኑ የሥርአተ ጾታ እና አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ጋር በመሆን ስልጠናው እንዲዘጋጅ መደረጉን ገልጸዋል ፡፡የባለሥልጣኑን ራእይና ተልእኮ ከማሳካት አንፃር በባለሥልጣኑ ከፍተኛውን የአመራርነት ቁጥር ይዘው የሚገኙ ሴቶችን የአመራርነት ግንዛቤ ፣ ክህሎትና ብቃት በማሳደግ ረገድ የሥልጠናው ፋይዳው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ሥልጠናውን የሰጡት በኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት የሥልጠና አማካሪ የሆኑት አቶ ጩና ቡያ በበኩላቸው ስለ አመራርነት ጽንሰ ሀሳብ ፣ታሪካዊ አመጣጥ፣ በተቋማት ውስጥ መሪ ያስፈለገበት ምክንያት ፣ስለ ልቦና ውቅር ፣እራስን ስለመግራት እና መግዛት፣ስለ ውጤታማ የሥራ ቡድን ምስረታ፣ስለውሳኔ አሰጣጥ፣የለውጥ ሂደት፣ሌሎችን ስለማብቃት እና ማሰልጠን ግልጽ፣ሳቢ እና አሳታፊ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡ ሠልጣኞችንም ለነበራቸው መልካም የሥልጠና ስነምግባር እና ተሳትፎ አመስግነዋል፡፡ በስልጠናው የተሳተፉ ሴት አመራሮች እና ከፍተኛ ባለሙያዎች ስልጠናው አቅማቸውንና ክህሎታቸውን ያዳበረ ግንዛቤያቸውንም ያሳደገ፣ ወቅቱን የጠበቀ የተሰጣቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ለሚያደርጉትን ጥረት ከፍተኛ አቅም የሚፈጥር እና ተነሳሽነታቸውን የሚጨምር መሆኑን ገልጸው አሰልጣኙ ያለውን ከፍተኛ የማሰልጠን ብቃት ፣አቅም እና ዘዴ አድንቀዋል፡፡ በሌሎች ጉዳዮችም ላይ በዚህ መልኩ ታስቦበት እና ታቅዶ በቂ ጊዜ እና በጀት ተመድቦ የአቅም ግንባታ ስልጠና የመስጠትና ሴቶችን የማብቃት ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ የተሰጠውን ሥልጣና መሠረት በማድረግ የባለሥልጣኑን ራዕይ እና ተልእኮ ለማሳካት በመግባባት፣አመለካከታቸውን በማስተካከልና በመለወጥ የራሳቸውን አቅም በመገንባት፣ ከስራቸው የሚገኙ ባለሙያዎችን በማብቃት እንዲሁም የባለሥልጣኑ ተገልጋዮችን በቅንነት፣በልበ ሰፊነት በርህራሄ ፣ በአስተዋይነት ፣በእርጋታ እና በሰከነ መንፈስ ለማገልገል ቃል ገብተው ፤ የኢትዮጵያን ህዝባዊ መዝሙር በጋራ በመዘመር ፤ ለመቄዶንያ አረጋውያንና አእምሮ ህሙማን መርጃ ማእከል በስልጠናው ተሳታፊዎች ስም ድጋፍ በማድረግ የስልጠና ሥልጠና መረሀ ግብሩ ፍጻሚ ሆኗል፡፡ በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ