ለሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት ጉዳዩ፦ ከኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ፈቃድ ባገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሩ 2018ዓ.ም አጋማሽ የመውጫ ፈተና ስለሚፈተኑ ተማሪዎች ብቁ እጩ ተፈታኞች የማጣርያ መስፈርቶች ይመልከታል፤

ለሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት ------------------------------------- ጉዳዩ፦ ከኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ፈቃድ ባገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሩ 2018ዓ.ም አጋማሽ የመውጫ ፈተና ስለሚፈተኑ ተማሪዎች ብቁ እጩ ተፈታኞች የማጣርያ መስፈርቶች ይመልከታል፤ ----------------------------------------------------------------------------------------------- የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ከተሰጡት ስልጣንና ተግባራት መካከል አንዱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራትን ጠብቀው እንዲሰሩ የመከታተል እና የመቆጣጠር ስራዎችን ያከናውናል፡፡ በዚሁ መሰረት የሁሉም ከባለስልጣኑ ፈቃድ ባገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሩ ተማሪዎች ተመርቀው ወደ ስራ ከመግባታቸው በፊት የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና ተፈትነው ማለፍ ያለባቸው በመሆኑ ብቁ እጩ ተፈታኝ ሆኖ ለመቅረብ እነዚህን መስፈርቶች መሟላት ኣለባቸው፦ 1. የተማሩብት ተቋም የተሰጠውን #ፈቃድ ጊዜ፣የትምህርት መስክ እና ካምፓስ ማረጋገጥ፤ 2. በትምህርት ላይ ቆይታቸው #አራት ዓመት ለሚጠናቀቅ የትምህርት መስኮች ** በመደበኛ እና ርቀት መርሃ ግብር በትምህርት መስኩ እስከ የካቲት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ፈቃድ የተሰጣቸው ተቋማት እና የተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ እስከ የካቲት 30 ቀን 2014 ዓ.ም መሆኑን ማረጋገጥ፤ ** ለኤክስቴሸን መርሃ ግብር በትምህርት መስኩ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ፈቃድ የተሰጣቸው ተቋማት እና የተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2014 ዓ.ም መሆኑን ማረጋገጥ፤ 3. የትምህርት ላይ ቆይታቸው #በአምስት ዓመት ለሚጠናቀቅ የትምህርት መስኮች ** በመደበኛ መርሃ ግብር በትምህርት መስኩ እስከ የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ፈቃድ የተሰጣቸው ተቋማት እና የተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ እስከ የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም መሆኑን ማረጋገጥ፤ ** ለኤክስቴሸን መርሃ ግብር በትምህርት መስኩ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ፈቃድ የተሰጣቸው ተቋማት እና የተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም መሆኑን ማረጋገጥ፤ 4. የትምህርት ላይ ቆይታቸው #ስድስት ዓመት (ዶ/ር ኦፍሜዲስን) ለሚጠናቀቅ የትምህርት መስኮች ** በመደበኛ መርሃ ግብር በትምህርት መስኩ እስከ የካቲት 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ፈቃድ የተሰጣቸው ተቋማት እና የተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ እስከ የካቲት 30 ቀን 2012 ዓ.ም መሆኑን ማረጋገጥ፤ 5. የተፈታኝ ሙሉ ስም እስከ አያት መኖሩን ማረጋገጥ፤ 6. የተማሪዎች ወደ ተቋሙ በዝውውር የመጡ ካሉ የዝውውር ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ 7. ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በቀረቡት የመውጫ ፈተና ተፈታኞች መረጃ በትምህርት መስኮችና በካምፓሶች የስነስርዓት ጥሰት የሌላቸው መሆኑ ማረጋገጥ፤ 8. በሚያዝያ 2013 ዓ.ም በየሁለት ደረጃ የመልቀቅያ ውጤት ወይም የ12 ክፍል ውጤት የተለቀቀበት ወቅት መሰረት በማድረግ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ላይ ቆይታቸው ማለት #በአምስት ዓመት ለሚጠናቀቅ የትምህርት መስኮች ** በመደበኛ መርሃ ግብር በትምህርት መስኩን እስከ የሰኔ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ፈቃድ የተሰጣቸው ተቋማት እና የተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ እስከ የሰኔ 30 ቀን 2013 ዓ.ም መሆኑን ማረጋገጥ፤ 9. ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሶፍትዌር ቴምፒሌቱ የሚያቀርቡት የመውጫ ፈተና ተፈታኞች መረጃ በባለስልጣኑ የተመራቂ ተማዎች መረጃ ቋት በማስገባት የትምህርት ማስረጃ ለማረጋገጥ አገልግሎት የሚሰጥበት በመሆኑ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ትክክለኛና ታማኝ መረጃ በተሟላ ሁኔታ እንደያቀርቡ ከፍተኛ ሃላፊነት ያለባቸው መሆኑ አውቀው ይህ ሳይሆን ሲቀር ደግም ባለስልጣኑ ሀላፊነት የማይወስድ መሆኑ እናሳስባለን፡፡