በከፍተኛ እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት የክትትልና ቁጥጥር መመሪያ 987/2016 መሠረት አሳሳች ማስታወቂያ የሚያሰራጭ ተቋምን በተመለከተ:-
በከፍተኛ እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት የክትትልና ቁጥጥር መመሪያ 987/2016 መሠረት አሳሳች ማስታወቂያ የሚያሰራጭ ተቋምን በተመለከተ:- ** ማንኛውም ተቋም በካምፓስ፣ በመርሀ ግብር ወይም በትምህርት መስክ ከባለስልጣኑ የከፍተኛ ትምህርት አገልግሎት ለመስጠት ፈቃድ ሳያገኝ ማንኛውንም ማስታወቂያ መስራትና ማሰራጨት የተከለከለ ነው፤ ** ከላይ የተጠቀሰውን ተላልፎ የተገኘ ተቋም ማስታወቂያውን ባስነገረበት መንገድ ማስተካከያ አድርጎ በአንድ ወር ውስጥ ለህዝብ ይፋ በማድረግ ለባለስልጣኑ ሪፖርት እንዲያደርግ ይደረጋል፤ የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያም ይሰጠዋል፤ ** ከላይ በተጠቀሰውን መሠረት ተግባራዊ ባያደርግ ተቋሙ የተሳሳተ ማስታወቂያ ባስነገረበት ካምፓስ፣መርሀ- ግብር ወይም የትምህርት መስክ ለ2 ዓመታት የከፍተኛ ትምህርት አገልግሎትእንዳይሰጥ ቅጣት ይጣልበታል፤ እና ** ከላይ የተጠቀሰውን የተላለፈ ተቋም የተሳሳተ ማስታወቂያ ባስነገረበት ካምፓስ ወይም መርሀ-ግብር ወይም የትምህርት መስክ እንዲዘጋ ይደረጋል፡፡ የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ ።
