#ማሳሰቢያ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት ጉዳዩ፦ በ2018 ዓ.ም አጋማሽ ለሚሰጠው የመዉጫ ፈተና ውይይት ስለሚኖር እንድትሳተፉ ስለማሳወቅ፤

#ማሳሰቢያ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት --------------------------------------------- ጉዳዩ፦ በ2018 ዓ.ም አጋማሽ ለሚሰጠው የመዉጫ ፈተና ውይይት ስለሚኖር እንድትሳተፉ ስለማሳወቅ፤ --------------------------------------------------------------------------------------------- በ2018 ዓ.ም አጋማሽ ለሚሰጠው የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና የተፈታኞችን ምዝገባ ለማካሄድ ይረዳን ዘንድ ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ ተማሪዎችን መረጃ ለመሰብሰብ የሚያስችል የሶፍት ዌር ቴምፕሌት የተዘጋጀ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለትምህርት ሚኒስቴር በቀን 2/04/2018 ዓ/ም በቁጥር 01//ተ _21/01/1090/18 በተፃፈ ደብዳቤ የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና በአመቱ አጋማሽ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡ በዚሁ መሰረት የተፈታኞች ምዝገባ ከ 6 _ 13/04/2018ዓ/ም ለማካሄድ የታቀደ በመሆኑ አስፈታኝ ለሆኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት 04/04/2018 ዓ/ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ በበይነ መረብ የሚሰጥ አጠቃላይ ኦሬንቴሽን ስለሚኖር የሚመለከታቸው እንዲገኙ እንዲደረግልን በማለት አሳውቋል፡፡ ስለሆነም የመውጫ ፈተና መረጃ ማስገቢያ ሲስተምን በተመለከተ 04/04/2018 ዓ/ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ Online ስልጠና ስለሚሰጥ ከታች በተቀመጠ Meeting Link በኩል በሰዓቱ ተገኝታችሁ አስፈላጊውን መረጃ እንድትወስዱ እንገልጻለን።