ማሳሰቢያ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት
ጉዳይ፡- የመመሪያና ስታንዳርዶች ረቂቅ ሰነድ ውይይት ላይ እንድትገኙ ስለመጋበዝ ባለስልጣኑ የከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት የጥራት ኦዲት መመሪያና ስታንዳርዶች ረቂቅ ሰነድ አዘጋጅቶ ግብዓት ለመሰብሰብ ለሁሉም ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የላከ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም በረቂቅ ሰነዶቹ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ለማድረግ እቅድ የተያዘ በመሆኑ ጥር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በአዲስ አበባ በሚገኘው ስካይ ላይት ሆቴል በሚካሄደው የውይይት መድረክ የሚሳተፍ የተቋሙ ባለቤት ወይም የበላይ ኃላፊ የሆነ አንድ ተሳታፊ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት እንድትልኩ እያሳወቀን ሙሉ ወጪያችሁን በራሳችሁ የምትሸፍኑ መሆኑን እናሳስባለን፡፡ በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ