በከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተቋም እና የፕሮግራም አሰጣጥ እውቅና መመሪያ 991/2016 መሠረት ስለ እውቅና ልዩ ግምገማ እና ውስን ግምገማ

በከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተቋም እና የፕሮግራም አሰጣጥ እውቅና መመሪያ 991/2016 መሠረት ስለ እውቅና ልዩ ግምገማ እና ውስን ግምገማ --------------------------------- --------- ---------------------------------------------------------------------------------------- #ስለ_ልዩ_ግምገማ የእውቅና ግምገማ በልዩ ሁኔታ ግምገማ እንዲካሄድ የሚያስገድዱ ሁኔታዎች፡- ** ሚኒስትሩ ወይም አግባብነት ያለው አካል የትምህርት ስርዓቱን በፖሊሲ ወይም አግባብነት ባላቸው ህጎች ሲያሻሽለው፤ ** ለተቋሙ የተሰጠው የተቋም ወይም ፕሮግራም እውቅና ጉድለት አለበት ተብሎ በመረጃና ማስረጃ የተደገፈ ጥቆማ የሚቀርብ ከሆነ፡፡ #ስለ_ውስን_ግምገማ ውስን የእውቅና ግምገማ እንዲካሄድ የሚያስገድዱ ሁኔታዎች፡- ** ተቋሙ ወይም ፕሮግራሙ በሁኔታ የተገደበ እውቅና ያለው ሆኖ በሪፖርቱ ላይ የተገለጹትን የጥራት ጉድለቶች ስለማሻሻሉ በግምገማ ለማረጋገጥ፤ ** በሪፖርቱ ላይ የተገለጹትን የጥራት ጉድለቶች ስለማሻሻሉ በግምገማ በማረጋገጥ በሁኔታ የተገደበ የተቋሙን ወይም የፕሮግራሙን እውቅና ወደ ሙሉ እውቅና ለማሳደግ፡፡ የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።