በየደረጃው የሚገኙ የባለሥልጣኑ አመራሮች የተቋሙን የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ገመገሙ

በየደረጃው የሚገኙ የባለሥልጣኑ አመራሮች የተቋሙን የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ገመገሙ -------------------------------------------------------------------------- ከጥር 14 እስከ 15 ቀን 2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ በበጀት ዓመቱ በባለሥልጣኑ ሊሰሩነ የታቀዱ ዋና ዋና ግቦችን መነሻ በማድረግ በየስራ ክፍሎቹ የተከናወኑ ተግባራት በዝርዝር ቀርበው ውይይት እና ግምገማ ተደርጎባቸዋል:: በግምገማ መድረኩ የተቋማት ፈቃድ አሰጣጥና የጥራት ኦዲት፤ የእውቅና እና ስታንዳርዳይዜሽን ፤የተቋማት ቁጥጥር፣ኢንስፔክሽን እና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ ፤የሥራ አመራር እና የአስተዳደር ዘርፎች በበጀት ዓመቱ ሊሰራቸው የታቀዱ ዋና ዋና ግቦችን መነሻ በማድረግ በየስራ ክፍሎቹ የተከናወኑ ተግባራት በዝርዝር በየሥራ ክፍሉ ኃላፊዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል:: ባለሥልጣኑ ባለፉት ስድስት ወራት በርካታ ውጤታማ ተግባራትን እንዳከናወነ የተገመገመ ሲሆን በተለይም በፈቃድ አሰጣጥና የጥራት ኦዲት ዘርፍ በዳግም ምዝገባ ተቋማት ራሳቸውን እንዲፈትሹ እና ያለባቸውን ክፍተት እንዲለዩ እና ጠንክረው እንዲሰሩ ማስቻሉን ፣የጥራት ኦዲትን አስመልክቶ በተቋማት እና በህብረተሰቡ ዘንድ ያለው ግንዛቤ እያደገ መምጣቱ፤ የፓይለት ኦዲት ሥራው ተጠናቆ እና ስርዓት ተዘርግቶ ወደ ኦዲት ስራ መገባቱ እና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና እና የአጠቃላይ ትምህርት ፈቃድ አሰጣጥ ላይ የተሰሩ ስራዎች አፈጻጸም ያደገ መሆኑ፤ በእውቅና እና ስታንዳርዳይዜሽን ዘርፍ ስለእውቅና አሰጣጥ ያለው ግንዛቤ መዳበሩ፣በርካታ ተቋማት የፕሮግራም እውቅና ይሰጠን የሚል ጥያቄ ማቅረባቸው እና የእውቅና አሰጣጥ ስራን ዲጂታላይዝ ማድረግ በመቻሉ ተገቢ ያልሆነ ስነ ምግባርን በማስቀረት ተዓማኒነቱን ከፍ ማድረግ መቻሉ እና ለ15 የፕሮግራሞች እውቅና መሰጠቱ እንዲሁም በባለሥልጣኑ የስታንዳርዳይዜሽን ስራ ግንዛቤ በመፍጠር ረገድ የተሻለ አፈጻጸም ማሳየቱ ፤ በተቋማት ቁጥጥር፣ኢንስፔክሽን እና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ ዘርፍ የተቋማት የክትትልና ቁጥጥር ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉ እና የኢንስፔክሽን ስራው በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ እየተሰራ ያለው ስራ አፈጻጸም ጥሩ ደረጃ ላይ ያለ መሆኑ እንዲሁም የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና የአቻ ግመታ አገልግሎት አሰጣጥን መሻሻል በመቻሉ ከበርካታ የመንግስት እና የግል ተቋማት የሠራተኞቻችን የትምህርት ማስረጃ ይረጋገጥልን ጥያቄ መቅረቡ እና በህብረተሰቡ ዘንድ ያለው በግል የራስን ትምህርት ማስረጃ የማረጋገጥ ፍላጎትና ተነሳሽነት በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩ እንዲሁም ባለስልጣኑ ከመሶብ የአንድ ማእከል አገልግሎት ጋር በመቀናጀት ለበርካታ የትምህርት ማስረጃዎች ማረጋገጫ የሰጠና እና የአቻ ግመታ ስራ ያከናወነ መሆኑ፤ በስራ አመራር እና በአስተዳደር ዘርፉም የተቋሙ ዋና ዋና ዘርፎች በመደገፍ ውጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻል የተሰሩ ስራዎች ጥሩ አፈጻጸም ፤ የባለሥልጣኑን ተቀባይነት ከፍ ለማድረግ የሚያስችለው የውስጥ ጥራት ኦዲት ስራ ጥሩ ደረጃ ላይ መድረስ እንዲሁም የኤንፎርሜሽ ቴክኖሎጂ የሥራ ክፍል መጠናከር እና በባለሥልጣኑ የሚሰጡ አገልግሎቶችን እና በባለሥልጣኑ የሚሰሩ ሥራዎችን ዲጂታላይዝ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉ በውይይቱ እና በግምገማ መድረኩ ከታዩት መካከል ይጠቀሳሉ:: የግምገማ መድረኩን የመሩት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አህመድ አብተው እያንዳንዱን ተግባር ከግቦቻችን አንጻር እያነጻጸርን በትኩረት ማየት ይገባናል ያሉ ሲሆን በዚህ ረገድ ያሳለፍናቸው ስድስት ወራት ሀገራዊ ፋይዳቸው ከፍ ያሉ ተግባራትን ያከናወንበትና የተሻለ ውጤት ያሳየንበት ነበር ብለዋል::አክለውም በየስራ ክፍሎቹ የተስተዋሉ ውስንነቶችን ፈጥነን በማረምና ጥሩ ውጤት ያመጣንባቸውን ደግሞ አጠናክሮ በማስቀጠል የተጣለብንን ሀገራዊ ትልዕኮ ይበልጥ ለማሳካት መስራት ይኖርብናል ብለዋል:: በግምገማ መድረኩ ከባለስልጠኑ ዋና ዳይሬክተር እስከ ቡድን መሪዎች ድረስ የሚገኙ የሥራ ኃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል:: የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ::