በጥራት ኦዲት መመሪያ እና ስታንዳርድ፤በዓለም አቀፍ ፣በማኅበረሰብ፣ለትርፍ ያልተቋቋሙ እና የበጎ አድራጎት ትምህርት ቤቶች የፈቃድ እና ፈቃድ እድሳት፤የህብረተሰብ ጤና፣የፋርማሴ እና የሜዲካል ላብራቶሬ ስታንዳርድ ረቂቅ ላይ ውይይት ተካሄደ

ታህሳስ 26 ቀን 2017 ዓ.ም በአዳማ ከተማ የባለሥልጣኑ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች በተገኙበት በጥራት ኦዲት መመሪያ እና ስታንዳርድ፤በዓለም አቀፍ ፣በማኅበረሰብ፣ለትርፍ ያልተቋቋሙ እና የበጎ አድራጎት ትምህርት ቤቶች የቅድመ መደበኛ ፣የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ የፈቃድ እና ፈቃድ እድሳት፤የህብረተሰብ ጤና፣የፋርማሴ እና የሜዲካል ላብራቶሪ ስታንዳርድ ረቂቅ ላይ ውይይት ተካሄዷል:: የጥራት ኦዲት መመሪያ እና ስታንዳርድ ረቂቅ በባለሥልጣኑ የጥራት ኦዴት መሪ ስራ አስፈጻሚ በሆኑት በወ/ሮ ትግስት ኃ/ስላሴ፤ የዓለም አቀፍ ፣የማኅበረሰብ፣ለትርፍ ያልተቋቋሙ እና የበጎ አድራጎት ትምህርት ቤቶች የቅድመ መደበኛ ፣የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ የፈቃድ እና ፈቃድ እድሳት ስታንዳርድ ረቂቅ በባለሥልጣኑ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና እና አጠቃላይ ትምህርት ፈቃድ አሰጣጥ መሪ ስራ አስፈጻሚ በሆኑት በወ/ሮ መቅደስ ደረሰ፤ የህብረተሰብ ጤና፣ የፋርማሴ እና የሜዲካል ላብራቶሪ ስታንዳርድ ረቂቅ በባለሥልጣኑ የእውቅና አሰጣጥ መሪ ሥራ አስፈጻሚ በሆኑት በአቶ ተረፈ በላይ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ፡፡ በውይይቱ ላይ ለተነሱ ሐሳቦች ፣አስተያየት እና ጥያቄዎች በባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አህመድ አብተው፤የእውቅና እና ስታንዳርዳይዜሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ድንኳና ንጉሳ፤ የተቋማት ፈቃድ አሰጣጥና የጥራት ኦዲት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ውብሸት ታደለ እና የተቋማት ቁጥጥር ኢንስፔክሽን እና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ኤሮ ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አህመድ አብተው በመመሪያው እና ስታንዳርዶቹ ላይ የተነሱ አስተያየቶችን በግብአትነት መውሰድ እንደሚገባ ገልጸው በባለሥልጣኑ የሚዘጋጁ መመሪያዎች እና ስታንዳርዶች የትምህርትን ጥራት በማረጋገጥ ላይ የተመሠረቱ እና ያተኮሩ መሆን እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ