አጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ እና የተከናወኑ ተግባራት

በሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 515/2014 አጠቃላይ ትምህርት ማለት በሀገሪቱ በቅድመ መጀመሪያ ደረጃ፣ በመጀመሪያ ደረጃ፣ በሁለተኛ ደረጃ መደበኛ እና መደበኛ ባልሆነ የትምህርት መርሀ ግብር የሚሰጥ ትምህርት ነው። (በሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 515/2014 አንቀጽ2 ንዑስ አንቀጽ 3) የዓለም ዓቀፍ፣ የማህበረሰብ፣ ለትርፍ ያልተቋቋመና የበጎ አድራጎት ትምህርት ቤቶች ፈቃድ አሰጣጥ እና እድሳት መመሪያ ቁጥር 992/2016 አንቀጽ 2 ከንኡስ አንቀጽ 11 እስከ 15 እና 17 መሠረት፡- ** በኢትዮጵያ የውጭ ሀገር ማህበረሰብ ትምህርት ቤት" ማለት በኢትዮጵያ የሚኖሩ የአንድ ሌላ ሀገር ዜጎች ልጆቻቸውን በሀገራቸው ስርዓተ ለማስተማር የሚያቋቁሙት ትምህርት ቤት ሆኖ በኢትዮጵያ ውስጥ ባለ በዚያ ሀገር ኤምባሲ ወይም ቆንስሊ ፅ/ቤት ባለቤትነት ወይም እውቅና የተቋቋመ ነው። ** “በውጭ ሀገር የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ትምህርት ቤት” ማለት በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወይም ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተቋቁሞ በኢትዮጵያ ስርዓተ ትምህርት መሠረት የትምህርት አገልግሎት የሚሰጥ ነው። ** “ዓለምአቀፍ ትምህርት ቤት” ማለት በኢትዮያ ውስጥ የሚቋቋም ዓለም አቀፍ ምዝገባ፣ ሥርዓተ ትምህርት፣ ምዘና እና የጥራት ቁጥጥር ያለውና ተግባራዊ የሚያደርግ ሆኖ በኢትዮጵያ ውስጥ የትምህርት አገልግሎት ለመስጠት አግባብ ካለው አካል ፍቃድ የተሰጠው ትምህርት ቤት ነው። ** “በውጭ ባለሃብት የተቋቋመ ትምህርት ቤት” ማለት በውጭ ባለሃብት ወይም የውጭ ካፒታል ወደ ኢትዮጵያ በማስገባት ኢንቨስት ያደረገ የውጭ ሀገር ዜጋ ወይም ሙሉ በሙሉ በውጭ ሀገር ዜጋ ባለቤትነት የተያዘ ድርጅት ወይም ከሃገር ውስጥ ባለሀብት ጋር በቅንጅት ኢትዮጵያ ውስጥ በተቋቋመ ድርጅት ኢንቨስት ያደረገ የውጭ ሀገር ዜጋ ወይም ድርጅት ሲሆን እንደ ውጭ ባለሀብት መቆጠር የፈለገ መደበኛ ነዋሪነቱ በውጭ ሀገር የሆነ ኢትዮጵያዊን ይጨምራል። ** "የበጎ አድራጎት ትምህርት ቤት" ማለት በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሠረት በተቋቋመ በጎ አድረጎት ድርጅት የሚቋቋም ትምህርት ቤት ሲሆን ለጠቅላላ ህዝብ ወይንም ለሶስተኛ ወገንመስራትን ዓላማ አድርጎ የተቋቋመ ትምህርት ቤት ነው። ** “ለትርፍ ያልተቋቋሙ ትምህርት ቤት" ማለት ለትርፍ ያልሆነ በግለሰብ ወይም ማህበራት ወይም በህብረት ስራ ማህበራት ወይም በሲቪክ ማህበራት ወይም አግባብነት ባለው ህግ የተመሰረተ ወይም በውጭ ሀገር ተመስርቶ በኢትዮጵያ ውስጥ ፈቃድ አግኝቶ የሚንቀሳቀስና በትምህርት ቤቱ ስም የሚገኙ ሀብቶችን በሙሉ ለመማር ማስተማር ስራው ብቻ የሚጠቀም የትምህርት ተቋም ነው።  እስካሁን በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት ** ለዓለም አቀፍ፣ ለማህበረሰብ፣ ለበጎ አድራጎት እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ትምህርት ቤቶች የፈቃድና የፈቃድ እድሳት መስፈርት ማዘጋጀት እና መከለስ፤ ** ለዓለም አቀፍ፣ ለማህበረሰብ፣ ለበጎ አድራጎት እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ትምህርት ቤቶች የፈቃድና የፈቃድ እድሳት ግምገማ ማካሄድ፤ ** በዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች የትምህርት ቤቱ የወላጅ ተማሪ መምህር ህብረት ሲመረጥ በታዛቢነት በመገኘት ግልጽ እና ፍትሀዊ ምርጫ መደረጉን መታዘብ፤ ** በዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች የ2018 ዓ.ም የትምህርት ክፍያ ጭማሪ ውይይት በሚደረግብት ጊዜ በታዛቢነት በመገኘት ውይይቱ በሰላማዊ መንገድ መካሂዱን መታዘብ፤ ** ከውጭ ሀገር ለሚመጡ መምህራን የሥራ ፈቃድ የድጋፍ ደብዳቤ ለስራና ክህሎት ሚኒስቴር መጻፍ እና ** ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ በዓለም አቀፍ እና የማህበረሰብ ትምህርት ቤቶችን ያሉ የተማሪዎችንና የመምህራንን መረጃ የማደራጀት ስራዎች ተሰርተዋል። የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።