በ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት እና ግምገማ ተካሄደ
የባለሥልጣኑ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም በአዳማ ከተማ የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት እና ግምገማ አካሄደዋል፡፡ የተቋማት ፈቃድ አሰጣጥና የጥራት ኦዴት ዘርፍ በባለሥልጣኑ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና እና አጠቃላይ ትምህርት ፈቃድ አሰጣጥ መሪ ስራ አስፈጻሚ በሆኑት በወ/ሮ መቅደስ ደረሰ፣ የከፍተኛ ትምህርት ፈቃድ አሰጣጥ መሪ ስራ አስፈጻሚ በሆኑት በወ/ሮ ህይወት አሰፋ እና በባለሥልጣኑ የጥራት ኦዴት መሪ ስራ አስፈጻሚ በሆኑት በወ/ሮ ትግስት ኃ/ስላሴ ፤የተቋማት ቁጥጥር ኢንስፔክሽን እና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ ዘርፍ በባለሥልጣኑ የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና አቻ ግመ መሪ ስራ አስፈጻሚ በሆኑት በአቶ ሀብታሙ ገ/መድህን፤ በእውቅና አሰጣጥ ዘርፍ በባለሥልጣኑ የእውቅና አሰጣጥ መሪ ሥራ አስፈጻሚ በሆኑት በአቶ ተረፈ በላይ ፤የስራ አመራር ዘርፍ በባለሥልጣኑ የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ በሆኑት በወ/ሮ ጥሩወርቅ ታደሰ እና የአስተዳደር ዘርፍ በባለሥልጣኑ የጽ/ቤት ኃላፊ በሆኑት በአቶ ዝናቡ ሀምሳሉ የ6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እና ግምገማ ተካሄዷል፡፡ በውይይቱ ላይ ለተነሱ ሐሳቦች ፣አስተያየት እና ጥያቄዎች በባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አህመድ አብተው፤የእውቅና እና ስታንዳርዳይዜሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ድንኳና ንጉሳ፤ የተቋማት ፈቃድ አሰጣጥና የጥራት ኦዴት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ውብሸት ታደለ እና የተቋማት ቁጥጥር ኢንስፔክሽን እና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ኤሮ ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አህመድ አብተው ማጠቃለያ እና የሥራ መመሪያ አቅጣጫ ሰጥተው የውይይት እና የግምገማ መድረኩ ተጠናቋል፡፡ በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ