ማስታወቂያ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት ጉዳዩ፦በጥር ወር 2017 ዓ.ም ለሚሰጠው የመዉጫ ፈተና ውይይት ስለሚኖር እንድትሳተፉ ስለማሳወቅ፤
በ2017 ዓ.ም ለሚሰጠው የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና የተፈታኞችን ምዝገባ ለማካሄድ ይረዳን ዘንድ ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ ተማሪዎችን መረጃ ለመሰብሰብ የሚያስችል የሶፍት ዌር ቴምፕሌት በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ታህሳስ 28/2017 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ላይ የሚጀምር ትምህርት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የሶፍት ዌር ቴምፕሌት አጠቃቀም ዙርያ ላይ በzoom meeting ማብራርያና ገለፃ ስለሚደረግ እንድትሳተፉ እያሳሰብን የzoom meeting link ቀደም ብሎ የሚለቀቅ ይሆናል፡፡ በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ