የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ፣ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እና የህክምናና ጤና ሳይንስ ሙያ ማህበራት የከፍተኛ ትምህርትና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የእውቅና አሰጣጥ ስርዓትን ዲጂታላይዝ ለማድረግ ተስማሙ

ታህሳስ 22 ቀን 2017 ዓ.ም የድሬዳዋ ዩነቨርሲቲ በኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የመሰብሰቢያ አዳራሽ የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ሙያ ማህበራት የእውቅና አሰጣጥ ስርዓትን ዲጂታላይዝ ለማድረግ የሚያስችል የኮንትራት ስምምነት ተፈጽሟል፡፡ በባለሥልጣኑ የእውቅናና ስታንዳርዳይዜሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ድንኳና ንጉሳ በስምምነቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ባለሥልጣኑ እውቅና ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማመልከቻ አስገብተው ግምገማ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኦባህ አደም በበኩላቸው የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የትምህርትና ስልጠና ጥራትን ለማረጋገጥ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ እና ከኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነት መደረጉ እንዳስደሰታቸው ገልጸው በስምምነቱ መሰረት በተቀመጠው ጊዜ ገደብ እና የጥራት ደረጃ ስራዎችን ጨርሶ ለማስረከብ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ የሚድዋይፈሪዎች ማኅበር ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢብራሂም ይመር ብቁና ተወዳዳሪ ባለሙያዎችን ለማፍራት የእውቅና አሰጣጥ ሥራ በአግባቡ መስራት አስፈላጊ በመሆኑ የኢትዮጵያ የሚድዋይፈሪዎች ማኅበር ከኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ጋር በመሆን የሚጠበቅበትን ድጋፍ ሁሉ ለማድረግ ይሰራል ብለዋል፡፡ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሶፍትዊር ማበልጸግ ቡድን መሪ አቶ ጌትነት ቶሎሳ እና በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሶፍትዊር ማበልጸግ ባለሙያ አቶ አንድነት አሰፋምእንደ ባለሙያ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለተለያዩ ተቋማት ሶፍትዊር በማበልጸግና አገልግሎት ላይ እንዲውል በማድረግ ውጤታማ ስራ ማስመዝገቡን ገልጸው ከባለስልጣኑ ጋር በሚከናወነው የእውቅና አሰጣጥ ስርዓትን ዲጂታላይዝ የማድረግ ሥራ ከቡድናቸው ጋር በመሆን ውጤታማ ስራ ለመስራት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡ በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ