ለባለድርሻ አካላት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ፤ክትትል እና ቁጥጥር መመሪያ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
ለኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ተጠሪ የሆኑ በፌደራል መንግስት ለተቋቋሙ ፤መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች እና ከውጭ በመጡ ባለሀብቶች ለተቋቋሙ የቴክኒክና ሙያ የትምህርትና ስልጠና ተቋማት ባለቤቶች እና ተወካዮች የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ፤ክትትል እና ቁጥጥር መመሪያ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ህዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም በባለሥልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተሰጠ ፡፡ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ ፈቃድ እና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ መመሪያ እና ስታንዳርዶች በባለሥልጣኑ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ፈቃድ ዴስክ ኃላፊ በሆኑት በአቶ ብርሃነመስቀል መላክ፤ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የክትትልና ቁጥጥር መመሪያ በባለሥልጣኑ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የክትትልና ቁጥጥር ባለሙያ በሆኑት በዶ/ር ታምራት ሀይሌ እና የክትትል ቼክ ሌስት የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የክትትልና ቁጥጥር ዴስክ ኃላፊ በሆኑት በአቶ ግሩም መኮንን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች የተቋማት ፈቃድ አሰጣጥ እና የጥራት ኦዲት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ውብሸት ታደለ እና በባለሥልጣኑ የተቋማት ቁጥጥር፣ ኢንስፔክሽ እና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ኤሮ ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ በስልጠና መረሀ ግብሩ ማጠቃለያ ላይ የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የተቋማት ቁጥጥር፣ ኢንስፔክሽ እና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ኤሮ ሰልጣኞች በስልጠናው ላይ ለነበራቸው ንቁ ተሳትፎ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ