የባለሥልጣኑ አመራሮች እና ሠራተኞች 19ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን አከበሩ
የባለሥልጣኑ አመራሮች እና ሠራተኞች 19ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን አከበሩ “ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት!!''በሚል መሪ ሐሳብ በባለሥልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ ህዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም በተከበረውን በዓል ላይ ተገኝተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት እና በዓሉን በንግግር የከፈቱት በባለሥልጣኑ የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ጥሩወርቅ ታደሰ እንዳሉት የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በሀገራችን ታሪክ የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ብዝሃነት ሕገ መንግሥታዊ ዋስትና ያገኝበት እና የተረጋገጠበት እለት መሆኑን ገልጸው ይህን ታላቅ ሀገራዊ በዓል ስናከብር ወንድማማችነትን በማጠናከር የበልጽግናች ጉዞችንን በማፋጠን መሆን አለበት ብለዋል፡፡ የእለቱን የመወያያ ሰነድ ያቀረቡት በባለሥልጣኑ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዝናቡ ሀምሳሉ በበኩላቸው ህብረ-ብሄራዊ ፌደራል ስርዓት በኢትዮጵያ ተግዳሮቶች እና የመፍትሄ ሃሳቦች ስለ ፌዴራሊዝም ጽንሰ ሐሳብ ፤የፌደራል ሥርዓት አስፈላጊነት በኢትዮጵያ ፤ በኢትዮጵያ እየተተገበረ ያለው የፌዴራሊዝም ስርዓት ያመጣው መልካም አጋጣሚ እና እየገጠሙት ያሉትን ፈተናዎች በመግለጽ የፌደራሊዝም ሥርዓት እንደ ሀገራች ያሉ ብዝሃ ማንነት፣ ሃይማኖት፣ቋንቋ፣ ባህል ፣ ሀብት፣ የቆዳ ሰፋት እና የህዝብ ብዛት ያላቸው አብዛኞቹ ሀገራት የሚከተሉት ስርዓት መሆኑን በሰፊው አብራርተዋል ፡፡ በቀረበው የመወያያ ሰነድ ላይ የተለያዩ አስተያየቶች እና ሃሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፤ ለተነሱት አስተያየት እና ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸው የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል ፡፡ በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ