የባለሥልጣኑ አመራሮች እና ሠራተኞች የህልም ጉልበት ለእምርታዊ እድገት በሚል ርዕስ ላይ ተወያዩ

የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አመራሮች እና ሠራተኞች ብልፅግና ፓርቲ የተመሠረተበት አምስተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ "የህልም ጉልበት፤ ለእምርታዊ እድገት" በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ህዳር 10 ቀን 2017 ዓ.ም በባለሥልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት አካሄዱ፡፡ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ ሰነዱ በሀገር ደረጃ እንዲከናወኑ በእቅድ የተያዙ ስራዎችን መሠረት ያደረገ በመሆኑ ሁሉም ሠራተኛ ግንዛቤ በመያዝ በዘርፉ እንዲሁም በሀገር ደረጃ የሚጠበቀውን እድገት ለማስመዝገብ በትጋት መስራት አለበት ብለዋል፡፡ የመወያያ ሰነዱን ያቀረቡት በባለሥልጣኑ የተቋማት ቁጥጥር፣ኢንስፔክሽን እና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ኤሮ ሲሆኑ በውይይቱ የብልፅግና ፓርቲ አመሠራረት፤ ተግዳሮቶችና ትሩፋቶች እንዲሁም ቀጣይ ጉዳይ አመላካች፣ ሀገራዊ መግባባት ለመፍጠርና የሀገረ መንግስት ቅቡልነትን ለማሳደግ የሀገራዊ ፓርቲ አስፈላጊነት፣ የጋራ ህልምን መረዳትና ማሳካት እና የመንግስት ሠራተኛውን ሚና በሚሉ ርዕሶች ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች የእውቅናና ስታንዳርዳይዜሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ድንኳና ንጉሳ ፤ የተቋማት ፈቃድ አሰጣጥ እና የጥራት ኦዲት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ውብሸት ታደለ እና የተቋማት ቁጥጥር፣ኢንስፔክሽን እና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ኤሮ የውይይት ሰነድ መሠረት በማድረግ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ