የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና አቻ ግመታ መመሪያ ቁጥር 990/2016 መሠረት በባለሥልጣኑ ማረጋገጫ የማይሰጣቸው የትምህርት ማስረጃዎች፡-

**ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ የደረጃ 4 ብቃት ማረጋገጫ(COC) ሳያሟሉ እየተማሩ የነበሩና ትምህርት ከጀመሩ በኋላ ያሟሉ ከሆኑ፤ **ፈቃድ በሌለው የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተማሩ ከሆነ፤ **የፕሮግራም ፈቃድ በሌለው የትምህርት መስክ የተማሩ ከሆነ፤ **የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ ሳያሟሉ የተማሩ ከሆነ፤ **የመጀመሪያ ዲግሪ ተምሮ ለመመረቅ የሚያስፈልገውን ዓመትና Credit hours ሳያሟሉ የተመረቁ ከሆነ እና **ከውጭ ሀገር ተምረው በኢፊዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የአቻ ግምት ሳያሰሩ ተምረው የተመረቁ ከሆነ ናቸው፡፡ የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።