ጥብቅ ማሳሰቢያ ለቀጣሪ ድርጅቶች በሙሉ!
አንዳንድ ቀጣሪ ድርጅቶች ከባለሥልጣኑ ያልተረጋገጠ የትምህርት ማስረጃን በትምህርት ተቋማት ብቻ በማረጋገጥ ህጋዊ አድርገው እየተጠቀሙ እንደሆነ ተቋማችን ደርሶበታል፤ በመሆኑም የትምህርት ማስረጃ የማረጋገጥ ኃላፊነት በሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 515/2014 አንቀጽ 6 ንዑስ አንቀስ 6 እንዲሁም ይህን ለማስፈጸም በወጣው የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና አቻ ግመታ መመሪያ ቁጥር 990/2024 መሠረት ለኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ብቻ የተሰጠ ሥልጣን በመሆኑ፤ ከባለሥልጣኑ ውጪ የሚረጋገጡ የትምህርት ማስረጃዎች ፍጹም ተቀባይነት የሌላቸው መሆኑን እየገለጽን በዚህ ተግባር የተሰማራችሁ ቀጣሪ ድርጅቶች ከድርጊታችሁ እንድትታቀቡ እያሳሰብን የትምህርት ማስረጃ ትክክለኛነትና ህጋዊነትን ማረጋገጥ የባለሥልጣን መ/ቤቱ ስልጣን ብቻ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን። የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።