የባለሥልጣኑ አመራሮች እና ሠራተኞች በፌዲራል መንግስት የ2017 የመጀመሪያ 100 ቀን እና በባለሥልጣኑ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ላይ ተወያዩ
የባለሥልጣኑ አመራሮች እና ሠራተኞች በፌዲራል መንግስት የ2017 የመጀመሪያ 100 ቀን እና በባለሥልጣኑ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ላይ ተወያዩ ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም በባለሥልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ የባለሥልጣኑ አመራሮች እና ሠራተኞች በፌዲራል መንግስት የ2017 የመጀመሪያ 100 ቀን የሪፎርም እና ዋና ዋና የኢኮኖሚ አፈጻጸም እንዲሁም በባለሥልጣኑ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡ በባለሥልጣኑ የተቋማት ቁጥጥር፣ኢንስፔክሽን እና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ኤሮ የ2017 የመጀመሪያ 100 ቀን የሪፎርም እና ዋና ዋና የኢኮኖሚ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ በውይይት መድረኩ የባለሥልጣኑ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በባለሥልጣኑ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ በሆኑት በወ/ሪት አመለወርቅ ደሳለኝ ቀርቧል፡፡ የቀረቡትን የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶች መነሻ በማድረግ በባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ ፤ በባለሥልጣኑ የተቋማት ቁጥጥር፣ ኢንስፔክሽ እና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ኤሮ እና የእውቅናና ስታንዳርዳይዜሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ድንኳና ንጉሳ ከባለሥልጣኑ ሠራተኞች ለተነሱ ጥያቄዎች ፣ሐሳቦች እና አስተያየቶች ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቶ የውይይት መድረኩ ተጠናቋል፡፡ በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ