17ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በባለሥልጣኑ ተከበረ

በኢፊዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን ፣ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!”በሚል መሪ ቃል 17ኛው የብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ጥቅምት 4ቀን 2017ዓ.ም በባለሥልጣኑ ቅጥር ግቢ ውስጥ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ ፡፡ ዕለቱን የተመለከቱ መልእክቶችን በማስተላለፍ፤ በሉዓላዊነት መገለጫና በህብረ ብሔራዊ አንድነት ምልክት በሆነው ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ፊት ቃለ-መሀላ በመፈጸም እና ብሔራዊ መዝሙር በመዘመር በዓሉ ተከብሮ ውሏል፡፡ በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ