ማሳሰቢያ

በኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የሶስተኛ ሳምንት የዳግም ምዝገባ ሥራ በበዓል ምክንያት ዓርብ መስከረም 24 እና ቅዳሜ መስከረም 25 ቀን 2017 ዓ.ም የማይኖር ሲሆን የአራተኛ ሳምንት የዳግም ምዝገባ ሥራ ሰኞ መስከረም 27ቀን 2017 ዓ.ም የሚቀጥል መሆኑን እንገልጻለን፡፡ በዚህ ሊንክ http://bit.ly/4do4ZUJ በተገለጸላችሁ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት በባለስልጣኑ ቅጥር ግቢ በመገኘት እንድትመዘገቡ እያሳሰብን በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ሆኖ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት በዳግም ምዝገባ ሂደት ውስጥ ያልገባ ተቋም መምሪያው ላይ በተቀመጠው አንቀጽ 2(11)መሠረት ከባለሥልጣኑ የወሰደው የማስተማር ፈቃድ በገዛ ፈቃዱ እንዳቋረጠ ተቆጥሮ ፈቃዱ የሚነጠቅ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡ በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ