ማሳሰቢያ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት በትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ቋት የተማሪዎች መረጃ ማስገባትን ይመለከታል

ባለሥልጣኑ የዳግም ምዝገባ መምሪያ አዘጋጅቶ እና አጸድቆ ሀምሌ 22/2016ዓ.ም ለባለድርሻ አካላት በማሳወቅ ወደ ስራ መግባቱ የሚታወቅ ነው፡፡ በወቅቱም ሁሉም የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለትምህርት ሚኒስቴር እና ለባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ አስፈላጊውን ተቋማዊ መረጃ መረጃ ማስገባት እንደሚጠበቅባቸው መገለጹ የሚታወስ ነው፡፡ ባለሥልጣኑ በመጀመሪያው ዙር የዳግም ምዝገባ ሂደት ላይ ሁሉንም የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በወጣላቸው የመመዝገቢያ ጊዜ ሰሌዳ መሰረት ከመስከረም 7/2017 ጀምሮ በመመዝገብ ላይ ይገኛል፡፡ የዳግም ምዝገባው የሰነድ ማሰባሰብ ሂደት እንደተጠናቀቀም በቀጣይ የሰነድ ምርመራና የመስክ ግምገማ ይደረጋል፡፡ በዚሁ መሰረት የመስክ ጉብኝት የሚደረግላቸው ተቋማት ባለስልጣኑ የሰነድ ምርመራ ካደረገ በኋላ ለመስክ ምልከታው ብቁ ሆነው የተገኙ ተቋማት እና በትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ቋት ውስጥ በመስፈርቱ መሰረት ተቋማዊ መረጃቸውን ያስገቡት ተቋማት ብቻ የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡ ስለሆነም በትምህርት ሚኒስቴር የHEMIS የመረጃ ቋት ውስጥ ተቋማዊ መረጃ ያላስገባ ማንኛውም ተቋም በባለሥልጣኑ የማይጎበኝና መስፈርቱን እንዳላሟላ ተቆጥሮ ፈቃዱ የሚነጠቅ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡ በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ