#ከኢፌዲሪ_ትምህርትና_ስልጠና_ባለሥልጣን_የተሰጠ_ማሳሰቢያ
በማንኛውም የትምህርት መስክ ከዲፕሎማ ጀምራችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ ለተማራችሁ የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ አገልግሎት ፈላጊዎች በሙሉ፤ በየካቲት 2016 ዓ.ም ጸድቆ ሥራ ላይ በዋለው የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥና የአቻ ግመታ መመሪያ ቁጥር 991/2016 መሠረት የሙያ ብቃት ምዘናን በተመለከተ፡- 1. እስከ 2009 ዓ.ም መጨረሻ ባለው ጊዜ ውስጥ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ተምረው የጨረሱ ያለ ብቃት ምዘና የትምህርት ማስረጃቸው ይረጋገጥላቸዋል፤ 2. በ2008 ዓ.ም የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርታቸውን የጀመሩ ዲግሪያቸውን ከማረጋገጣቸው በፊት የደረጃ አራት የሙያ ምዘና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ (በመማር ላይ እያሉ ያገኙት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት/COC/ ተቀባይነት ይኖረዋል) 3. ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬቶች ተማሪው የመጀመሪያ ዲግሪውን ለመማር ከመመዝገቡ በፊት የተጠናቀቁ መሆን አለባቸው፡፡ የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ