Skip to content
Newsroom

ማሳሰቢያ

ETA Education & Training Authority September 25, 2024 1 min read
ማሳሰቢያ
በኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የሁለተኛ ሳምንት የዳግም ምዝገባ ሥራ ሰኞ መስከረም 13 ቀን 2017 ዓ.ም ተጀምሮ የቀጠለ ቢሆንም በበዓል ምክንያት ሐሙስ መስከረም 16 እና ዓርብ መስከረም 17 ቀን 2017 ዓ.ም የዳግም ምዝገባ ሥራ የማይኖር መሆኑን እና ቅዳሜ መስከረም 18 ቀን 2017 ዓ.ም የሁለተኛ ሳምንት የዳግም ምዝገባ ሥራ የሚቀጥል መሆኑን እንገልጻለን፡፡ በዚህ ሊንክ http://bit.ly/4do4ZUJ በተገለጸላችሁ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት በባለስልጣኑ ቅጥር ግቢ በመገኘት እንድትመዘገቡ እያሳሰብን በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ሆኖ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት በዳግም ምዝገባ ሂደት ውስጥ ያልገባ ተቋም መምሪያው ላይ በተቀመጠው አንቀጽ 2(11)መሠረት ከባለሥልጣኑ የወሰደው የማስተማር ፈቃድ በገዛ ፈቃዱ እንዳቋረጠ ተቆጥሮ ፈቃዱ የሚነጠቅ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡ በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ
News Announcement
Share